10 በርካታ ባህር ሰርጓጅ መርከብ ያላቸው ሀገራት
በባህር ውስጥ ከእይታ ተሰውረው ሚሳኤል የሚያስወነጭፉ ባህር ሰርጓጅ መርከከቦች ባለቤት መሆን በአለማቀፍ ውሃማ አካላት የበላይነትን ለመያዝ ወሳኝ ነው
በአለማችን 43 ሀገራት ከ460 በላይ ባህር ሰርጓጅ መርከቦች እንዳሏቸው ይነገራል
ሆላንዳዊው ኮርኔልስ ድሬቤል በ17ኛው ክፍለ ዘመን የመጀመሪያዋን ባህር ሰርጓጅ መርከብ መስራቱ ይታመናል።
ሞላላ ቅርጽ ያላቸው ባህር ሰርጓጅ መርከቦች ሲያሻቸው በባህር ላይ የሚቀዝፉ፤ ሲፈልጉ ደግሞ ወደ ባህር ውስጥ ሰርገው በመግባት ከእይታ መሰወር የሚችሉ ናቸው።
ባህር ሰርጓጅ መርከቦች በባህር ውስጥ ጥናትና ምርምር ለማድረግና ለተለያዩ የባህር አሰሳ ስራዎች ይውላሉ።
ከዚህም ባሻገር ያለምንም ድምጽና እይታ በባህር ውስጥ በመጓዝ ወታደራዊ ግዳጆችን ለመፈጸም ሁነኛ መሳሪያ ሆነው ያገለግላሉ።
ሚሳኤሎች እና ቶርፒዶዎችን የሚታጠቁ ባህር ሰርጓጅ መርከቦች ባለቤት መሆን በአለማቀፍ ውሃማ አካላት የበላይነትን ለመያዝ ወሳኝ መሆኑ ይነገራል።
የግሎባል ፋየር ፓወር መረጃ እንደሚያሳየው በአለማችን 43 ሀገራት ከ460 በላይ ባህር ሰርጓጅ መርከቦች አሏቸው።
በ65 ባህር ሰርጓጅ መርከብ ቀዳሚ የሆነችው ሩሲያ፤ ስምንት በኒዩክሌር የሚሰሩ ባህር ሰርጓጅ መርከቦችን እየሰራች ነው ተብሏል።
አሜሪካ ሁሉም ባህር ሰርጓጅ መርከቦቿ በኒዩክሌር ሃይል የሚሰሩ ናቸው፤ ይህም ውሃ ውስጥ ለወራት ከእይታ ተሰውረው መቆየት ያስችላቸዋል።
በርካታ ባህር ሰርጓጅ መርከቦች ያሏቸውን ሀገራት ይመልከቱ፦