ሩሲያ “የውሃ ክልሌን የጣሰ የአሜሪካ የባህር ሰርጓጅ መርከብ አሳድጄ አባረርኩ” አለች
አሜሪካ መርከበቿ የሩሲያ የውሃ ክልልን ጥሰው አልገቡም በማለት አስተባብላች
ሩሲያ እና አሜሪካ ከሰሞንኛው የዩክሬን ጉዳይ ጋር በተያያዘ መካረር ውስጥ ገብተዋል
ሩሲያ የውሃ ክልሏ ጥሶ የገባን የአሜሪካ የሰርጓጅ መርከብ አሳዳ ማባረሯን ከሰሞኑ አስታውቃለች።
ኢንትራፋካስ የዜና ወኪል የሩሲየ መከላከያ ሚኒስቴርን ጠቅሶ እንደዘገበው፤ የሩሲያ ባህር ኃይል መርከቦች የአሜሪካ ባህር ኃይል ሰርጓጅ መርከብን በፓስፊክ ከሚገኝ የሩሲያ የውሃ ክልል አሳደው አስወጥተዋል።
ሩሲያ ይህንን ያደረገቸው የአሜሪካ ሰርጓጅ መርከብ ከውሃ ስር ወጥቶ ላይኛው የውሃ ክፍል ላይ እንዲሳፈፍ ተሰጠውን ትእዛዝ ባለመቀበሉ እንደሆነም ዘገባው አመላክቷል።
ይህንን ተከትሎም ሩሲያ፤ ዋሽንግተን ዓለም አቀፍ ህግን በመጣስ በሀገሬ ብሄራዊ ደህንነት ላይ አደጋን ደቅናለች በማለት አሜሪካን ከሳለች።
አሜሪካ ዛሬ በሰጠችው ምለሽ በሩሲያ የውሃ ክልል ውስጥ ምንመ አይነት እንቅስቃሴ አላደረኩም በማለት ከሩሲያ የቀረበባትን ከስ አስተባብላች።
የአሜሪካ ጦር ቃል አቀባይ ካፒቴን ካየል ራኒስ፤ “ሩሲያ አሜሪካ በውሃ ክልሌ ላይ ወታደራዊ እንቅስቃሴ አድርጋለች በማለት የምታቀርበው ክስ ከእውነት የራቀ ነው” ብለዋል።
አሁን ላይ የአሜሪካ መርከቦች ያሉበትን ቦታዎች አልናገርም፤ ነገር ግን በዓለም አቀፍ ውሃ አካላት ላይ መረከቦቻችን ያለምንም ገደብ ይንቀሳቀሳሉ ሲሉም ተናግረዋል።
አሜሪካ የውሃ ክልልን ሳትጥስ ከቅርብ ሆና የሌሎች ሀገራትን ወተደራዊ እንቅስቃሴ መከታተል የተለመደ ተግባሯ መሆኑ ይታወቃል።