በዚህ ውድድር የስፖርት ተሽከርካሪዎች አምራቹ ማክላረን ቀዳሚው ሆኗል
የአለማችን ፈጣን ተሽከርካሪዎች አምራች ኩባንያዎች የሚሳተፉበት አመታዊ ውድድር በብሪታንያዋ ሰሴክስ ከተማ ተካሂዷል።
ለሶስት ቀናት በቆየው የ“ጉድ ዉድ ፌስቲቫል ኦፍ ስፒድ” ውድድር 10ሩ የ2023 ፈጣን ተሽከርካሪዎች ተለይተዋል።
ሞተር ዋን ድረ ገጽ 3 ነጥብ 8 ኪሎሜትር የሚሸፍነውን ውድድር በፍጥነት ያጠናቀቁ 10 ተሽከርካሪዎችን ከነአሽከርካሪዎቹና የወሰደባቸው ጊዜ ይፋ አድርጓል።
በዚህም መሰረት የብሪታንያው የስፖርት ተሽከርካሪዎች አምራች ማክላረን ቀዳሚ ሲሆን ኒሳን እና ፎርድ በውድድሩ ለቀጣይ ተስፋ ሰጪ ውጤት አስመዝግበዋል ተብሏል።
በአመታዊ የፈጣን ተሽከርካሪዎች ውድድሩ ከ1 እስከ 10ኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ተሽከርካሪዎችን እንጠቁማችሁ፦
1. McLaren Solus GT (ብሪታንያ) - 45.34 ሰከንድ
2. Subaru GL Family Huckster (ጃፓን) - 46.38 ሰከንድ
3. McLaren-Cosworth M26 (ብሪታንያ) - 46.89 ሰከንድ
4. Porsche 911 GT3 Cup (ጀርመን) – 47.40 ሰከንድ
5. Nissan Skyline GT- R R32 (ጃፓን) - 48.18 ሰከንድ
6. Chrysler Viper GTS-R (አሜሪካ) - 49.29 ሰከንድ
7. Rimac Nevera (ክሮሺያ)- 49.32 ሰከንድ
8. Ford Puma WRC (አሜሪካ) - 49.47 ሰከንድ
9. Ferrari 488 Challenge (ጣሊያን) – 49.88 ሰከንድ
10. Porsche 911 GT2 RS Clubsport (ጀርመን) – 51.45 ሰከንድ