ቻይና ከሶስት ሺህ ዶላር በማይሞላ ገንዘብ የሚገዛ ባለ ሁለት ጋቢና ፒክ አፕ ተሽከርካሪ ሰርታለች
የዓለማችን የኢንዱስትሪ መዲና የሆነችው ቻይና በርካሽ ዋጋ የሚገዛ ባለ ሁለት ጋቢና ፒክ አፕ ተሽከርካሪ መስራቷን ገልጻለች።
ይህ ተሽከርካሪ ሶስት ሺህ ዶላር በማይሞላ ገንዘብ በርዎ ድረስ ይመጣሎታል የተባለ ሲሆን ተሽከርካሪ በኤሌክትሪክ ይሰራል ተብሏል።
የተሽከርካሪው አምራች ኩባንያ ከነማጓጓዣው ሶስት ሺህ ዶላር ብቻ ስከፍላል የተባለ ሲሆን ከወዲሁ የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።
ሺያን ማንጋ የተባለው የተሽከርካሪው አምራች ኩባንያ በአሊባባ የበይነ መረብ የግዢ አማራጭ መሰረት በ2 ሺህ 920 ዶላር ክፍያ ብቻ እስከ 20 ቀናት ውስጥ ለደንበኞቹ እያደረሰ ይገኛል ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።
ይሁንና ይህ ርካሽ ተሽከርካሪ የጥራት ጉድለቶች አሉበት የተባለ ሲሆን አነስተኛ ክብደት መያዙ፣ የመጫን አቅሙ እና ሌሎች የጥራት ጉድለቶች እንዳሉበት በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
እንዲሁም የአየር ማቀዝቀዣ እና ማሞቂያ፣ ከአደጋ መከላከያ የሖኑ እንደ ኤርባግ እና የመሳሰሉት ቁሳቁሶች የሉትም የተባለ ሲሆን የጎደሉትን ለማሟላት ተጨማሪ 320 ዶላር መክፈል ይጠበቅቦታል።
በሰዓት የመጓዝ አቅሙ 34 ኪሎ ሜትር ርቀት ብቻ ነው የጠባለ ሲሆን በአንድ ጊዜ ቻርጅ ደግሞ 100 ኪሎ ሜትር ብቻ እንደሆነ በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
አራት ሰዎችን የመጫን አቅም አለው የተባለው ይህ ተሽከርካሪ ጥራቱን የበለጠ ለማሳደግ ባትሪውን መቀየር እንደሚቻል ተገልጿል።