በዓለም አቀፍ ደረጃ ፊንላንድ በጣም ደስተኛ ሀገር ተሰኝታለች
የ2022 የዓለም አቀፍ የደስታ ሪፖርት ይፋ የተደረገ ሲሆን፤ የተለያዩ ሀገራት በሪፖርቱ ላይ ተዝርዝረዋል።
የዓለም የደስታ ሪፖርት ሀገራት ዜጎቻቸው ምን ያህል ደስተኛ እንደሆኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ የደስታ ሁኔታ ላይ ያተኮረ ጉልህ ጥናት ነው።
10ኛ ዓመቱን የደፈነው ሪፖርቱ፤ ሁለት ቁልፍ ሀሳቦች ላይ የተመሰረተ መሆኑም የተገለፀ ሲሆን፤ የበሀገራት ውስጥ ደህንነት እንዲሁም ሌሎች የህይወት ቁልፍ መለያዎች ላይ የተመሰረተ መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።
ጥናቱ ግለሰባዊ ደህንነትን በመለካት፤ የህይወት ግምገማዎች፣ አዎንታዊ ስሜቶች እና አሉታዊ ስሜቶች ላይ የተመሰረተ ነውም ተብሏል።
የዓለም አቀፍ የደስታ ሪፖርት 2022 በአጠቃላይ 150 ሀገራን ያጠቃለለ ሲሆን፤ የነፍስ ወከፍ ገቢ፣ ማህበራዊ ድጋፍ፣ የህይወት ምርጫዎችን የማድረግ ነፃነት፣ ልግስናና የሙስና አመለካከት ከመለኪያዎቹ መሀል ናቸው ተብሏል።
በዚህም መሰረት የ2022 የዓለም የደስታ ሪፖርት ሞሪሸስ በአፍሪካ ደስተኛዋ ሀገር ሆናለች።
ደሴቲቱ ሀገር ሞሪሽስ ከ10 ነጥብ ከስድስት በላይ አስመዝግባ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ 52ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።
አልጄሪያ፣ ኮንጎ፣ ኮትዲቯር፣ ሞሮኮ፣ ሞዛምቢክ በአፍሪካ ደስተኛ ህዝብ ያላቸው ሀገራት በመባል ከ2ኛ እስከ 6ኛ ያለውን ሰረጃ መያዛቸውም በሪፖርቱ ተመላክቷል።
ኢትዮጵያ አራት ነጥብ በማስመዝገብ 20ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። በሪፖርቱ ኢትዮጵያ ከናምቢያ ግብጽ በመቀጠል በደረጃው ግርጌ ከተቀመጡ ሀገራ መሀል ሆናለች።
በሪፖርቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ፊንላንድ በጣም ደስተኛ ሀገር መንበሩን እንደተቆጣጠረች ነው።