ልዩልዩ
ፓስፖርቶችን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘጋጁ ነበር የተባሉ 10 የኢሚግሬሽን ሰራተኞች ታሰሩ
ሰራተኞቹ ለውጭ አገራት ዜጎች ጭምር ፓስፖርት ሲሰጡ እንደነበር ተገልጿል
ሰራተኞቹ መንግስትን ከ1 ሚሊዮን በላይ ብር አክስረዋል ተብሏል
ፖሊስ ፓስፖርቶችን በህገ-ወጥ መንገድ ሲያዘጋጁ ነበር ያላቸውን 10 የኢሚግሬሽን ሰራተኞች አሰረ፡፡
የኢሚግሬሽን፣ የዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ሰራተኞች ናቸው የተባለላቸው አስሩ ሰራተኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።
የ5 አመት ህጻን አስገድዳ የደፈረችው ወጣት በእስር ተቀጣች
ተጠርጣሪዎቹ ህጋዊውን የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደት ወደ ጎን በመተው፣ የፓስፖርት ባለቤቶችን ሙሉ መረጃ በመቀየር እና በአንድ ማእከል መጠናቀቅ የነበረበትን አገልግሎት ወደ ተለያዩ ቅርንጫፎች በማዘዋወር ወንጀሉን በኔትወርክ መፈፀማቸውን በፌዴራል ፖሊስ የሙስና ወንጀሎች ዳይሬክተር ኮማንደር ታደሰ አያሌው ለኢቲቪ ገልፀዋል።
ተጠርጣሪዎቹ ከደላሎች ጋር በፈጠሩት የጥቅም ትስስር በወንጀል የሚፈለጉ ግለሰቦች እና የውጭ ሀገር ዜጎችም ጭምር ፓስፖርት እንዲያገኙ ከማስቻል ባለፈ መንግስት ሊያገኝ ይችል የነበረውን ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ እንዳሳጡም ነው ኮማንደር ታደሰ የተናገሩት።