ተከሳሿ በፈጸመችው የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የ33 ወራት እስር ተፈርዶባታል
እንደ ፍትህ ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ ተከሳሽ ጌጤ ባልቶሌ ትባላለች፤ የ20 ዓመት ወጣት ናት፡፡ በወንጀል ህጉ አንቀጽ 627/4/ለ ስር የተመለከተዉን ተላልፋ በፈጸመችዉ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ክስ ተመስርቶባት ጉዳዩ በክርክር ላይ ቆይቷል፡፡
ተከሳሽ ከእርሷ ጋር ተቃራኒ ጾታ ካለዉ የ5 ዓመት ህጻን ልጅ ጋር ሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 10፡00 ሰዓት ሲሆን እንዲሁም ከተጠቀሰዉ ቀን በፊትም በተለያዩ ቀናት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታዉ የካ አባዶ ኮንዶሚኒየም በሚገኘዉ መኖሪያ ቤት ዉስጥ በሞግዚትነት የምታሳድገዉን የ5 ዓመት ህጻን አይኑን በማሰር እና ስሜቱን በማነሳሳት የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል መፈጸሟን በማስረጃ በማረጋገጥ ክስ የተመሰረተ ስለመሆኑ የዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ ያስረዳል፡፡
“ህወሓት ወራሪ እንጂ ተጎጂ አይደለም”- ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ
ተከሳሽም ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የካ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት ቀርባ የእምነት ክህደት ቃሏን ስትጠየቅ ድርጊቱን ስለመፈጸሟ እንዲሁም ጥፋተኛ ስለመሆኗ በዝርዝር ያመነች በመሆኑ በተከሰሰችበት የወንጀል ድንጋጌ ስር የጥፋተኝነት ፍርድ ተላልፎባታል፡፡
በዚህም መሰረት ጥቅምት 02 ቀን 2014 ዓ.ም የዋለው ችሎት ተከሳሽ በ2 ዓመት ከ9 ወራት ጽኑ እስራት እንድትቀጣ ወስኖባታል ተብሏል፡፡