የኬንያው ሩቶ እና የደቡብ አፍሪካው ራማፎሳ ካጋሜ ከፍተኛ ሀብት ካካበቱት መሪዎች መካከል ተጠቅሰዋል
በአለማችን በርካታ መሪዎች ፖለቲካዊ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ከፍተኛ ሃብት ማካበታቸው ይነገራል።
ሀብት ያካበቱት መሪዎች ሀብታም ሀገራትን የሚመሩት ብቻ አይደሉም፤ በድህነት ውስጥ የሚገኙ ሀገራትን የሚመሩ ፕሬዝዳንቶችና ጠቅላይ ሚኒስትሮችም ባለጠጋ ናቸው።
መሪዎች ትክክለኛውን የሃብት መጠናቸውን ሚስጢራዊ የሚያደርጉት ቢሆንም ያሆ ፋይናንስ የተለያዩ ምንጮችን አጣቅሶ ለእውነት የቀረቡናቸው ያላቸውን ግምቶች ይፋ አድርጓል።
በዚህም የሩሲያው ፕሬዝዳንት በ200 ቢሊየን ዶላር ቀዳሚው የአለማችን ሀብታም መሪ መሆኑን ነው የገለጸው።
የቀድሞው የኬጂቢ ሰላይ ከአለማችን 10 ቢሊየነሮች ተርታ የሚያሰልፋቸውን ሀብት ማካበታቸውን የቀድሞው የሄርሚታጅ ካፒታል አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ቢል ብሮውደር ተናግረዋል።
በየካቲት ወር 2024 ህይወቱ ያለፈው አሌክሲ ናቫልኒ ፑቲንን በገንዘብ ወዳጅነታቸው ከሚወቅሱት መካከል ይጠቀሳል። ናቫልኒ የሩሲያው ፕሬዝዳንት በጥቁር ባህር ቅንጡ ቤተመንግስት እንዳላቸው ይናገራል።
ከ20 አመት በላይ በስልጣን ላይ ያሉት ፑቲን ግን ከሀብት ማጋበስ ጋር በተያያዘ የሚቀርብባቸውን ወቀሳ አይቀበሉትም።
የሩሲያ የምርጫ ኮሚሽን በ2018 ባወጣው መረጃ ፑቲን ከ2011 እስከ 2016 673 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ሀብት እንዳከበቱና በትውልድ ከተማቸው ሴንትፒተርስበርግ የመኖሪያ አፓርትመንት እና በሴንትፒተርስበርግ ባንክ 230 አክሲዮን እንዳላቸው ብቻ ነው የጠቀሰው።
የፑቲን ወዳጅ የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ሁለተኛውን ደረጃ ይዘዋል። ኪም በቻይና፣ ሩሲያ፣ ስዊዘርላንድ እና ሌሎች ሀገራት በቤተሰቦቻቸው በከፈቷቸው የባንክ ሂሳቦች ከ5 ቢሊየን ዶላር በላይ ሀብት አላቸው ተብሏል።
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና የደቡብ አፍሪካው ሲሪል ራማፎሳ ከፍተኛ ሀብት ካካበቱ የአለማችን 10 መሪዎች ውስጥ ተካተዋል።