በርካታ ባለጠጎች የሚገኙባችው የአፍሪካ ሀገራት
በአፍሪካ 21 ቢሊየነሮችና ከ135 ሺህ በላይ ሚሊየነሮች እንደሚገኙ የአፍሪካ ዌልዝ የ2024 ሪፖርት ያሳያል
የአህጉሪቱ 90 በመቶ ቢሊየነሮችና 56 በመቶ ሚሊየነሮች በአምስት ሀገራት የሚኖሩ ናቸው ተብሏል
በአህጉረ አፍሪካ ከ1 ሚሊየን ዶላር በላይ ሀብት ያላቸው 135 ሺህ 200 ሚሊየነሮች እንዳሉ የአፍሪካ ዌልዝ የ2024 ሪፖርት ያሳያል።
ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ሃብት ያስመዘገቡ ሚሊየነሮች (ሴንቲ ሚሊየነሮች) ቁጥርም 342 መድረሱን የሚያነሳው ሪፖርቱ፥ በአፍሪካ 21 ቢሊየነሮች እንዳሉም ያብራራል።
“ሄንሊ ኢኤንድ ፓርትነርስ” እና ኒው ወርልድ ዌልዝ በጋራ የሚያዘጋጁት አመታዊ ሪፖርት የአህጉሪቱ 90 በመቶ ቢሊየነሮችና 56 በመቶ ሚሊየነሮች በአምስት ሀገራት እንደሚኖሩ ያመላክታል።
ግብጽ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ናይጀሪያ፣ ኬንያ እና ሞሮኮ የባለጠጎች ሀገራት ናቸው።
በቢሊየነሮች ብዛት ግብጽ በሰባት ቀዳሚ ስትሆን በሴንቲ ሚሊየነሮች ብዛት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ ቀዳሚዋ ናት። በደቡብ አፍሪካ ከ37 ሺህ በላይ ሴንቲ ሚሊየነሮች ይገኛሉ።
የአፍሪካ ዌልዝ ሪፖርት ከፈረንጆቹ 2013 እስከ 2023 18 ሺህ 700 ባለጠጎች አፍሪካን ለቀው መውጣታቸውን ያሳያል።
በአሁኑ ወቅት በአለማቀፍ ደረጃ ትውልዳቸው በአፍሪካ የሆነ 54 ቢሊየነሮች ቢኖሩም መኖሪያቸውን በአፍሪካ ያደረጉት 21ዱ ብቻ ናቸው።
በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተወለደው ቢሊየነር ኤለን መስክን ጨምሮ በርካታ ትውልደ አፍሪካ ቢሊየነሮች በአሜሪካ፣ ብሪታንያ፣ አውስትራሊያ፣ ፈረንሳይና ሌሎች ሀገራት ይኖራሉ።