በአፍሪካ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ የቆዩ መሪዎች
ዴሞክራሲ አሁንም ዳዴ እያለ በሚገኝባት አፍሪካ ከቅኝ ግዛት በኋላ አንድ ግዜ ብቻ መሪ የቀየሩ ሀገራት ይኖሩባታል
የሞቱት ወይም በሀይል ከስልጣን የተወገዱት ሳይቆጠሩ በአሁኑ ወቅት ከሶስት እርት አመታት በላይ በስልጣን ላይ የዘለቁ አምስት መሪዎች አሉ
አፍሪካ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ የቆዩ መሪዎች
ብዙ የአፍሪካ መሪዎች በጉልበት፣ ህግን በመጣስ ወይም ህገ-መንግስቶችን ለራሳቸው እንዲመቻቸው አድርጎ በማሻሻል ስልጣን ላይ ሙጥኝ ማለት በዘመናዊው የአህጉሪቱ ታሪክ ውስጥ ሲተገበር የቆየ መደበኛ ሁነት ነው፡፡
ከሁለት እስከ አምስት አስርት ዓመታት ድረስ የቆዩት እነዚህ መሪዎች ተቋማትና ህግን የራሳቸው መጠቀሚያ በማድረግ በስልጣን ላይ ቆይተዋል።
መሪዎቹ ስልጣኝ በቃኝ በማለት አልያም ምርጫን ተከትሎ በስነስርአት ስልጣንን ለማስረከብ እምብዛም ፈቃደኛ አይደሉም፡
በዚህ የተነሳም የሞቱት ወይም በሀይል ከስልጣን የተወገዱት ሳይቆጠሩ በአሁኑ ወቅት ከሶስት እርት አመታት በላይ በስልጣን ላይ የዘለቁ አምስት መሪዎች አሉ፡፡
የተመረጡ ፕሬዚዳንቶች ከስልጣን ዘመናቸው በላይ ለመምራት እንደማይሞክሩ ለማረጋገጥ ጠንካራ ተቋማት ያሏቸው አገሮች ያስፈልጋሉ።
አፍሪካ ለረጅም ጊዜ በስልጣን ላይ የቆዩ በርካታ ፕሬዚዳንቶችን እና ንጉሶችን አይታለች።
አስገራሚው ነገር ደግሞ ከዚህ ሁሉ አመታት በኋላ መሪዎቹ አሁንም ከስልጣን ራሳቸውን ለማግለል ፍላጎት የላቸውም፡፡
በአሁኑ ወቅት በህይወት ከሚገኙ ለረጅም ጊዜ በመንበር ላይ ከሰነበቱ የአፍሪካ መሪዎች መካከል የኢኮቶሪያል ጊኒውን ፕሬዝዳንት የሚያህል የለም፡፡
ከፈረንጆቹ 1979 ጀምሮ ለአምስት አስርተ አመታት በተጠጋ ጊዜ 45 አመታትን በስልጣን ላይ የዘለቁት ቴዎዶሮ ኦቢያንግ ቀዳሚው ናቸው፡፡
እርሳቸውን በመከተል የ91 አመቱ አዛውንት የካሜሩኑ ፖል ቢያ የሚጠቀሱ ሲሆን እኚህ ፕሬዝዳንት ሀገራቸው ከፈረንሳይ እና እንግሊዝ ቅኝ ግዛት ከወጣችበት ከ1960ዎቹ መጀመርያ በኋላ ሀገሪቱ ያየቻቸው ሁለተኛ መሪ ሆነው ለ42 አመታት በስልጣን ዘልቀዋል፡፡
ኮንጎ ፣ የኡጋንዳ እና የኤርትራ መሪዎች ከ3 አስርት አመታት በላይ በአፍሪካ ሀገራት ስልጣን ላይ የዘለቁ ተጠቃሽ መሪዎች ናቸው፡፡