ኢኮኖሚ
በ2024 የአለማችን 10 ቀዳሚ ጥቁር ባለጠጎች
17 ጥቁር ቢሊየነሮች የፎርብስን የቢሊየነሮች ዝርዝር ቢቀላቀሉም ከጠቅላላው ድርሻቸው ከ1 በመቶ በታች ነው
አሜሪካዊው ዴቪድ ስቴዋርድ ናይጀሪያዊውን አሊኮ ዳንጎቴ በመብለጥ ቁጥር አንድ ጥቁር ቢሊየነር ሆነዋል
የአለማችን የቢሊየነሮች ቁጥር በ2024 2 ሺህ 781 ደርሷል።
አሃዙ በ2021 ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በ21 ያሻሻለ እና ከ2023 በ144 ብልጫ ያለው ነው።
የእነዚህ ባለጠጎች ሃብት ሲደመር 14 ነጥብ 2 ትሪሊየን የሚደርስ ሲሆን፥ አሜሪካ በ813፤ ቻይና ደግሞ በ473 ቢሊየነሮች ብዛት ከፊት ተቀምጠዋል።
በፎርብስ የ2024 ሪፖርት መሰረት 3 ሺህ ከሚጠጉት የአለማችን ባለጠጎች ውስጥ 17ቱ ብቻ ናቸው ጥቁር።
ከቀዳሚዎቹ 10 ጥቁር ቢሊየነሮች ውስጥ አምስቱ አሜሪካውያን ሲሆኑ፥ ሶስቱ ናይጀሪያውያን ናቸው።
በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሰማሩት አሜሪካዊ ዴቪድ ስቴዋርድ ናይጀሪያዊውን አሊኮ ዳንጎቴ በመብለጥ የአለማችን ቁጥር አንድ ጥቁር ቢሊየነር ሆነዋል።
የ2024 የፎርብስ ቀዳሚ 10 ጥቁር ቢሊየነሮችን ይመልከቱ፦