በ2022/23 780 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ እንደሚመረት ይጠበቃል
ምድራችን በስፋት ከምታበቅላቸው ስብሎች ስንዴ ከበቆሎ በመቀጠል ሁለተኛውን ደረጃ ይይዛል።
በ2022/23 የምርት አመትም 780 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ እንደሚሰበሰብ ይጠበቃል።
ቻይና 137 ነጥብ 7 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን ስንዴ በማምረት ቀዳሚውን ደረጃ እንደምትይዝም የስታስቲካ መረጃ ያመለክታል።
ቤጂንግ ቀዳሚዋ ስንዴ አምራች ሀገር ብትሆንም በየወሩ ከ1 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን በላይ ስንዴ ከተለያዩ ሀገራት ታስገባለች።
በዚህ አመት ከምግብ ፍጆታ ተርፎ ይከማቻል ተብሎ የሚጠበቀው ስንዴ 286 ሚሊየን ሜትሪክ ቶን እንደሚደርስ ይጠበቃል።