100 ሀገራት በኮሮና ላይ የቀረበውን የምርመራ ውሳኔ ሀሳብ ደገፉ
ቻይና ቀደም ብላ የዓለም ጤና ድርጅት ከሚያዘጋጀው ምርመራ ውጭ የሚመጣን የምርመራ ሀሳብ እንደማትቀበል ገልፃ ነበር፡፡
በአውስትራሊያ ግፊት ጭምር በአውሮፓ ህብረት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ዛሬ በጀመረው የዓለም ጤና ድርጅት ስብሳባ ላይ ይቀርባል
በአውስትራሊያ ግፊት ጭምር በአውሮፓ ህብረት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ዛሬ በጀመረው የዓለም ጤና ድርጅት ስብሳባ ላይ ይቀርባል
የሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአንድ ወቅት የቻይናውን መሪ ዥ ጂንፒንግን “ብቸኛው ጦረኛ” ብለው አድንቀዋቸው ነበር፡፡ ፑቲን እየቀለዱ ነበር፣ ነገርግን ያ አባባላቸው እያደር እውነት እየሆነ መጣ፡፡
ሩሲያ ዛሬ በሚካሄደው የዓለም የጤና ስብሰባ ላይ የሚቀርበውን በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ላይ ገለልተኛ ምርምራ ይደረግ የሚለውን የውሳኔ ሀሳብ የደገፉ100 ሀገራትን ተቀላቅላለች፡፡
በአውሮፓውያኑ የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ የመጣው፣አውስትራሊያ ቫይረሱ ሲከሰት ቻይና የያዘችበት መንገድ ይመርመር ብላ ግፊት እያደረገች ባለችበት ወቅት ነው፡፡
ቻይና በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ንዴቷን አንጸባርቃለች፤ ይህ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን አለምአቀፍ ጥረት የሚያበላሽ ነው በማለት አውስትራሊያን ከስሳለች፡፡
በአለም ጤና ድርጅት አመታዊ ስብስባ ላይ የሚቀርበው ይህ የውሳኔ ሀሳብ፤ ሀገር ነጥሎ በቻይና ላይ ወይም በሌላ ሀገር ላይ ይደረግ አይልም፡፡ ነገርግን ድርጅቱ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የወሰደው ምላሽ ገለልተኛ፣ ነፃና የተሟላ ምርመራ እንዲደረግ የውሳነ ሀሳቡ ይጠይቃል፡፡
የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ግን አውስትራሊያ በቻይና ላይ እንዲቀርብ ከምትፈልገው ምርመራ አንፃር ደካማ ነው ተብሏል፡፡ ይህ የአብላጫ የአለም ጤና ድርጅት አባል ሀገራን በተለይም ከቻይና ጋር ጠንካራ ግንኙነት ያላትን ሩሲያን ፊርማ የሚጠይቅ እንደሆነ እየተገለጸ ነው፡፡
ያ ማለት ግን የቻይና መንግስት በቀላሉ እጅ ይሰጣል ማለት አይደለም፡፡ የአውስትራሊያ መንግስት ምንጭ ለኤቢሲ አንደገለጸው በውሳኔ ሀሳቡ ላይ የቀረበው ቋንቋ በጣም ጠንካራ ነው፤ ይህም ዝርዝርና ትክክለኛ ምርመራ እንደሚደረግ ያረጋግጣል ብለዋል፡፡
ቻይና ቀደም ብላ በዓለም ጤና ድርጅት ብቻ የሚደረግ ምርመራን ብቻ እንደምትደግፍ ገልፃ ነበር፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት በቻይና ተጽእኖ አድሮበታል እየተባለ በግልጽ ሲከሰስ ነበር፡፡ ነገርግን የድርጂቱ ባለስልጣናት ይህን ክስ አይቀበሉትም፡፡
ባለፈው ሳምንት በዩናይትድ ኪንግደም የቻይና አምባሳደር ሊዩ ዢያ ሚንግ “ክፍት ነን፤ ግልጽም ነን፤ ምንም የምንደብቀው ነገር የለም፡፡ የምንፈራውም ነገር የለም፡፡ አለምአቀፍና ነፃ ግምገማን እንቀበላለን ነገርግን በዓለም ጤና ድርጅት የተዘጋጀ መሆን አለበት” ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ብዙ ሀገራት በአውሮፓ ህብረት የቀረበውን ውሳኔ ሀሳብ ላይ ፈርመዋል፡፡ ይህ ቻይና ማድረግ ከምትችለው ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡
ቻይና የውሳኔ ሀሳቡን ልትቀበል እንደምትችልም የሚያመላክቱ ነገሮች አሉ፡፡ የቻይና ሚዲያዎች እንደዘገቡት ከሆነ ፕሬዘዳንት ዥ ጅንፒንግ በስብሰባው መክፍቻ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ተብሏል፤ቁልፍ የሆነውን አጀንዳ ሊያልፉት አይችሉም የሚል ግምት ተሰጥቷል፡፡