የሕገ መንግስት ትርጉም ጉዳይ ረጅም ጊዜ አይወስድም- ስብሳቢ መአዛ አሸናፊ
ትርጉም አያስፈልግም ከተባለ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚቀርብና በዚህ ላይ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይግባኝ የማለት መብት እንዳለውም መሸናፊ ገልጸዋል
የጉባዔው አባላት በሙሉ ጊዜያቸው እየሰሩ ስለሆነ የትርጉሙ ጉዳይ ረጅም ጊዜ አንደማይወስድ የጉባኤው ሰብሳቤ መአዛ አሸናፊ አስታወቁ
የጉባዔው አባላት በሙሉ ጊዜያቸው እየሰሩ ስለሆነ የትርጉሙ ጉዳይ ረጅም ጊዜ አንደማይወስድ የጉባኤው ሰብሳቤ መአዛ አሸናፊ አስታወቁ
ሚያዚያ 28 ቀን 2012 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል የተባሉ አንቀጾች ለሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ እንዲላኩ መጽደቃቸው ይታወሳል፡፡
በዚህም መሰረት ጉባዔው ስራውን መጀመሩን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ ሰብሳቢ መኣዛ አሸናፊ አስታውቀዋል፡፡
“አባላቱ ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው በጉዳዩ ላይ እየሰሩ ነው” ያሉት ፕሬዚዳንቷ በመጀመሪያ ጉባዔው እነዚህን የመመለከት ሥልጣን አለው ወይስ የለውም በሚለው ላይ መወያየታቸውን ገልጸዋል፡፡
በዚህም መሰረት በተጠቀሱት አንቀጾች ላይ ሕገ መንግስታዊ ትርጉም የመስጠት ሥልጣን እንዳለው ጉባዔው የተስማማ መሆኑን ወ/ሮ መኣዛ አስታውቀዋል፡፡
አሁን ላይ ዕቅድ ወጥቶ እየተሰራ መሆኑንም ነው ፕሬዚዳንቷ በሰጡት መግለጫ ያስታወቁት፡፡በቀጣይ በስራዎቹ ላይ የሙያ አስተያየት መስጠት ሂደት እንደሚኖርና መድረክም እንደተመቻቸ ገልጸዋል፡፡
ጉዳዮ የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል ወይስ አያስፈልገውም የሚለው በቀጣይ እንደሚታይ የገለጹት የጉባዔው ሰብሳቢና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አንቀጾቹ ትርጉም ያስፈልግቸዋል ከተባለ ወደ ትርጉም ይኬዳል ነው የተባለው፡፡ በአንጻሩ ትርጉም አያስፈልግም ከተባለ የውሳኔ ሃሳብ እንደሚቀርብና በዚህ ላይ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ይግባኝ የማለት መብት እንዳለውም በመግለጫው ተነስቷል፡፡
ይህ ጉዳይ ረጅም ጊዜ እንደማይወስድ የተገለጸ ሲሆን የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ
አባላት ሙሉ ጊዜያቸውን ሰጥተው እየሰሩ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡
ከአባላቱ መካከል ሦስቱ ከፌዴሬሽን ም/ቤት የተወከሉ በመሆናቸው የገለልተኝነት ጉዳይ ጥያቄ አይኖረውም ወይ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ “ጫና ለመፍጠር የሚያስችል ሁኔታ የለም፣ሥራውን ሙያዊ በሆነ መልኩ ብቻ ነው የምንሰራው ” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የሕገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትና ምክትል ፕሬዚዳንትን ጨምሮ 11 አባላት ሲኖሩት ሦስቱ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት ናቸው፡፡
የሕገ መንግስት ትርጉም ያስፈልጋቸዋል የተባሉት አንቀጾች አንቀጽ 54 ንዑስ አንቀጽ 1፣ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 3 አንቀጽ እና 93 ናቸው፡፡