ቻይና ኮሮናን የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ አይገባም አለች
አንዳንድ ፖለቲከኞች ኮሮናን የጤና ጉዳይ ሳይሆን የፖለቲካ ጉዳይ አድርገውታል-የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ቻይና ዓለም ኮሮናን ለፖለቲካ መጠቀሚያ የሚያደርጉ አካላትን ሀሳብ ውድቅ እንዲያደርግ ጠየቀች
ቻይና ዓለም ኮሮናን ለፖለቲካ መጠቀሚያ የሚያደርጉ አካላትን ሀሳብ ውድቅ እንዲያደርግ ጠየቀች
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለፖለቲካ መጠቀሚያ የሚያደርጉ አካላትን ሃሳብ ውድቅ ማድረግ እንዲያደርግ ቻይና ጠየቀች፡፡
የቻይና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ይ እንደገለጹት አሁን ላይ የዓለም ስጋት የሆነውን ቫይረስ መከላከል እንጅ እርሱን የፖለቲካ መጠቀሚያ ማድረግ አይገባም፡፡
ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ከሀንጋሪ፣ቦሲኒያና ሄርዞጎቪኒያ እንዲሁም ከኢስቶኒያ አቻዎቻቸው ጋር በስልክ በተነጋገቱበት በተነጋገሩበት ወቅት ነው፡፡
ሀገራቱ ቻይና የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ባደረገችው ጥረት አጋነትን በማሳየታቸው ያመሰገኑት ሚኒስትር ዋንግ ይ አንዳንድ ፖለቲከኞ ግን ጉዳዩን የጤና ሳይሆን የፖለቲካ አድርገውታል ሲሉም ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ ቻይና የራሷን ችግር መፍታቷን የገለጹት ሚኒስትሩ ኮሮና የመከላከልና መቆጣጠር ልምድን ለሌሎች ሀገራት እናካፍላለን ብለዋል፡፡ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ዘር፣ቀለም፣ሀገርና ሌሎችንም የማይለይ በመሆኑ ዓለም በትብብር ሊታገለው የሚገባ መጥፎ ነገር ነው ብለዋል፡፡
ይህንን ገዳይ ቫይረስ ለመከላከል ደግሞ በትብብር መንፈስ መስራት ግደታ ስለመሆኑ ያነሱት የቻይናው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከዚህ በፊት ከነበረው በበለጠ ሀገራት ሊቀራረቡና ሊረዳዱ ይገባል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
በአንዳንድ ሀገራት ያሉ ፖለቲከኞች ወረርሽኙን ፖለቲካዊ እያደረጉ መሆኑን የጠቆሙት ዋንግ ቫይረሱን የሆነ አካል ብቻ አድርጎ ማየት፣የዓለም ጤና ድርጅትን ስም ጥላሸት መቀባትና ሌሎች አላስፈላጊ ነገሮችን ማድረግ ላይ ትኩረት አድርገዋል ብለዋል፡፡
እነዚህ ፍረጃዎች ዓለም አቀፍ የሞራል መርሆችን የጣሱ፣ዓለም ወረርሽን ለመከላከል እያደረገ ያለውን ጥረት የሚዲናቅፉ በመሆናቸው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ሊያወግዛቸው እንደሚገባ አሳስበዋል ዋንግ ይ፡፡
ቻይና አሁን እስካሁን 82 ሺ 933 ሰዎች በኮሮና መያዛቸውን የገለጸች ሲሆን ከ4ሺ 600 በላይ ደግሞ ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡የኮሮና ቫይረስን የፖለቲካ መጠቀሚያ አታድርጉት ያለችው ቻይና ምናልባትም ከአሜሪካ ጋር ያላትን እሰጥአገባ ለመጠቆም የተጠቀመችበት ሊሆን እንደሚችል የሚናገሩ ተንታኞች አሉ፡፡