ዩኤኢ የስደተኛ ቤተሰብ ላላቸው ልጆች ያደረገችው ድጋፍ የወንድማማችነት ተግባር ነው-ኮሚሽኑ
ዩኤኢ የስደተኛ ቤተሰብ ላላቸው ልጆች ያደረገችው ድጋፍ የወንድማማችነት ተግባር ነው-ኮሚሽኑ
የተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን ዛሬ እንዳስታወቀው እስካሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ስደተኞች በሚገኙባቸው ሰባት ክልሎችና በአዲስ አበባ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያና ድጋፍ የሚውል 7.6 ሚሊዮን ዶላር ወጭ ማድረጉን አስታውቋል፡፡
የኮሚሽኑ ተወካይ አን ኢንኮንትሬ ይሄን ያሉት የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ(ዩኤኢ) በኢትዮጵያ ለሚገኙ 100 ለሚሆኑ ስደተኛ ቤተሰብ ላላቸው ህፃናት የምግብ እርዳታ ባደረገችበት ወቅት ነው፡፡
የእርዳታው ተጠቃሚ ከሆኑ ህጻናት መካከል አብዛኞቹ ኤርትራውያን ናቸው ያሉት ተወካይዋ ለእርዳታው ኤምሬትስን አመስግነዋል፤በረመዳን ጾም ወቅት የሚደረግ የወንድማማችነት ተግባር ነው ብለዋል፡፡
ዩኤ.ኢ. ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚሆን 33 ሜትሪክ ቶን የሚሆን የእርዳታ ቁሳቁስ ልካ ነበር፡፡ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከዩ.ኤ.ኢ ለኢትዮጵያ ለተላከው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡
ከተላከው 33ሺ ቶን የድጋፍ ቁሳቁሶችን ውስጥ ለኢትዮጵያ 15 ሜትሪክ ቶን የሚሆነው የድጋፍ ቁሳቁስ ሲበረከት ቀሪው ለአፍሪካ ሀገራት እንደሚበረክት ተገልጾ ነበር፡፡
ዩ.ኤ.ኢ እየሰጠችው ያለው ድጋፍ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሚደረገውን አለምአቀፍ ጥረት ለማገዝ መሆኑን ገልጿለች፡፡