በናይጀሪያ ከባድ ዝናብ ባደረሰው ጉዳት ምክንያት ከ100 በላይ እስረኞች አመለጡ
የእስር ቤት አገልግሎቱ ከእስር ያለመጡትን እየፈለገ ሲሆን እስካሁን በሌሎች የጸጥታ አካላት ትብብር 10ሩ ተይዘዋል ተብሏል።
ከባድ ዝናብ በናይጀሪያ ዋና ከተማ አቅሪቢያ በሚገኘው የሱሌጃ እርስር ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ቢያንስ 118 እስረኞች ማምለጣቸውን የእስር ቤት አገልግሎት ቃል አቀባይ ተናግረዋል
በናይጀሪያ ከባድ ዝናብ ባደረሰው ጉዳት ምክንያት ከ100 በላይ እስረኞች አመለጡ።
ባለፈው ረቡዕ ሌሊት የጣለው ከባድ ዝናብ በናይጀሪያ ዋና ከተማ አቅሪቢያ በሚገኘው የሱሌጃ እርስር ቤት ላይ ጉዳት ማድረሱን ተከትሎ ቢያንስ 118 እስረኞች ማምለጣቸውን የእስር ቤት አገልግሎት ቃል አቀባይ ተናግረዋል።
ቃል አቀባዩ አዳሙ ዱዛ ሀሙስ እለት ባወጡት መግለጫ ለበርካታ ሰአታት የቆየው ከባድ ዝናብ ግርግዳውን እና በዙሪያው ያለውን ግንብ ጨምሮ የውስጠኛውን የእስርቤት ክፍል አፈራርሶታል ብለዋል።
የእስር ቤት አገልግሎቱ ከእስር ያለመጡትን እየፈለገ ሲሆን እስካሁን በሌሎች የጸጥታ አካላት ትብብር 10ሩ ተይዘዋል ተብሏል።
ዱዛ "ያለመጡጥን ለመያዝ በእልህ እያሳደድን ነው" ብለዋል።
ያመለጡትን ለመያዝ መንግስት ከፍተኛ ክትትል እያደረገ ነው ያሉት ዱዛ ህዝቡ በፍለጋው እንዲተባበር እና አጠራጣሪ ነገሮችን ሲያይ በአቅራቢያው ላለ የጸጥታ አካል እንዲጠቁም ጠይቀዋል።
ዱዛ ከእስር ያመለጡትን ግለሰቦች ማንነት በዝርዝር አልገለጹም፤ ነገርግን ቀደም ሲል የእስላማዊው የቦኮሀራም ታጣቂ ቡድን አባላት በሱሌጃ እስርቤት ይታሰሩ ነበር።
እስርቤቶች በተጨናነቁባት እና ልል የሆነ ጸጥታ ሁኔታ ባለባት ናይጀሪያ፣ እስርቤትን ሰብሮ ማምለጥ ዋና የጸጥታ ስጋት እየሆነ መጥቷል።
በቅርብ አመታት ውስጥ በደካማ መሰረተ ልማት እና በታጣቂዎች ጥቃት ምክንያት በሽዎች የሚቆጠሩ እስረኞች አምልጠዋል።
አይኤስ በ2022 ከፍተኛ ጥበቃ በሚደረግበት እስርቤት ላይ በፈጸመው ጥቃት 440 እስረኞች ነጻ መውጣታቸው በጉልህ የሚጠቀስ ነው።
እስር ቤቶቹ በቅኝ ግዛት ዘመን የተገነቡ በመሆናቸው ማርጀታቸውን እና ደካማ መሆናቸውን የገለጹት ቃል አቀባዩ እያንዳንዳቸው ሶስት ሺህ መያዝ የሚችሉ ስድስት እርቤቶች ግንባታን ጨምሮ እስርቤቶችን ለማዘመን ጥድፊያ ላይ ነን ብለዋል።