ለ22 ዓመት ታስሮ የቆየ እስረኛ ከእስር በሚፈታበት ቀን አመለጠ
እስረኛው በፖሊስ እየታደነ ሲሆን ለፈጸመው ወንጀል የአራት ዓመት እስር ይጠብቀዋል ተብሏል
በሩሲያ ህግ መሰረት ከእስር ቤት ያመለጠ እስረኛ ወደ እስር ቤቱ ከተመለሰ ምህረት ይደረግለታል
ለ22 ዓመት ታስሮ የቆየ እስረኛ ከእስር በሚፈታበት ቀን አመለጠ፡፡
ካሞልጆን ካሎኖቭ ከ22 ዓመት በፊት ነበር በግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ በህግ ቁጥጥር ስር የዋለው፡፡
በሩሲያዋ ኢርኩትስክ ግዛት ዚማ ከተማ ነዋሪ የነበረው ይህ ግልሰብ ወንጀለኛ ቡድን በማደራጀት፣ በዘረፋ እና ግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ የ22 ዓመት ፍርድም ይተላለፍበታል፡፡
የእስር ጊዜውን ጨርሶ በመፈቻው ዕለት ግን ከእስር ቤቱ ተገቢውን የህግ ሂደት ሳይከተል ማምለጡ ተገልጿል፡፡
በሩሲያ ህግ መሰረት አንድ እስረኛ ከታሰረበት ማረሚያ ቤት ቢያመልጥም በሶስት ቀናት ውስጥ ተመልሶ መምጣት ከቻለ በወንጀል የማይጠየቅ ሲሆን ይህ እስረኛ ግን ይህን እድል አልተጠቀመበትም ሲል ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል፡፡
ግለሰቡ አሁን ላይ ፖሊሶች እንዳይዙት ለመደበቅ የተለያዩ ሙከራዎችን በማድረግ ላይ እንደሆነ የተጠረጠረ ሲሆን የሀገሪቱ ፖሊስ እያደነው እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ከእስር ቤት በመፈቻው ቀን ማንንም ሳይሳውቅ የጠፋው ይህ እስረኛ በፖሊስ ተይዞ ፍርድ ቤት ከቀረበ የተጨማሪ አራት ዓመት እስር እንደሚጠብቀው ተገልጿል፡፡
እንዲሁም የአራት ዓመት የእስር ጊዜቀውን ከጨረሰ በኋላ ለግዳጅ ስራ ወደተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ይላካል የተባለ ሲሆን ከእስር ያመለጠው ግለሰብ እስካሁን ለምን እንዳመለጠ እና የት እንዳለ አልታወቀም ተብሏል፡፡