በምሸት መዝናኛ ክለብ በተፈጠረ የእሳት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 59 ሲደርስ የቆሰሉት ደግሞ ከ150 አለፈ
እሳቱ የተከሰተው በሰሜን መቄዶንያ በሚገኝ መዝናኛ ክለብ ላይ ነው

ጠቅላይ ሚኒስትር ሂርስቲጃን ሚኮስኪ "ይህ ለመቄዶንያ ከባድና በጣም አሳዛኝ ነው። የብዙ ወጣቶችን ህይወት ማጣት የማይጠገን ነው"ብለዋል
በሰሜን መቄዶንያ ኮካኒ ከተማ በሚገኘ የምሽት መዝናኛ ክለብ ላይ እሁድ ማለዳ በተከሰተ የእሳት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 59 ሲደረስ የቆሰሉት ደግሞ ከ150 አልፏል።
ከአደጋው ጋር በተያያዘ የመንግስት ባለስልጣናትንና ፐልስ የተባለው ክለብ ስራ አስኪያጅ ጨምሮ 20 ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር ውስጥ ሚኒስትሩ ፓንስ ቶስኮቭስኪ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
ሚኒስትሩ እንደገለጹት እሳቱ የተፈጠረው በሙዚቃ ድግስ ወቅት በተቀጣጣይ ቁስ አማካኝነት ነው።
"እሳቱ ከተያያዘ በኋላ በምሸት ቤቱ ውስጥ ተስፋፍቷል።" ሮይተርስ በመድረክ ላይ ሲጫወት የነበረው ባንድ በነጭ የእሳት ነበልባል ሲያያዝ የሚያሳየውን ቪዳዮ ትክክለኛነት ማረጋገጡን ዘግቧል።
የእሳቱ ነበልባል ወደ ላይ በመውጣት የቤቱን ጣራ አቀጣጥሎታል።
አንድ የሀገሪቱ ቴሌቪዥን የእሳት አደጋ ስራተኞች የነደደውንና እየጨሰ የነበረውን "ፐልስ" የተባለውን ክለብ መግቢያ በር ሲያጠፉ የሚሳይ ቪዲዮ ለቋል። ሮይተርስ ኤምአርቲ የተባለው የሰሜን መቄዶንያ ብሮድካስተር ጠቅሶ እንደዘገበው ደግሞ ከባድ የመቃጠል አደጋ የደረሰባቸው 27 ሰዎች በስኮፕጄ ሲቲ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ሲሆን ሌሎች 23 ደግሞ በክሊኒካል ሴንተር ህክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ። ከተጎጂዎች መካከል ልዶች እንደሚገኙበት ዘገባው ጠቅሷል።
እሳቱ በሀገሪቱ ሰአት አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 ሰአት ነው የተከሰተው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሂርስቲጃን ሚኮስኪ በፌስቡክ ገጻቸው "ይህ ለመቄዶንያ ከባድና በጣም አሳዛኝ ነው። የብዙ ወጣቶችን ህይወት ማጣት የማይጠገን ነው፤ በቤተሰቦቻቸው፣ በወዳጆቻቸውና በጓደኞቻቸው ላይ የደረሰው ጉዳት የማይለካ ነው"ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመለከታቸው ሀሉም የሀገሪቱ ተቋማት የቆሰሉትንና የተጓጂ ቤተሰቦችን እንዲረዱ ጥሪ አቅርበዋል።