ፖለቲካ
የአረብ ኢምሬትስ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ በአሜሪካ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው
የዱባይ ምክትል ገዥና የአረብ ኢምሬትስ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሼክ ታህኑን ቢን ዛይድ አልናህያን በነገው እለት በአሜሪካ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው

አረብ ኢምሬትስ የአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ ስትራቴጂካዊ አጋር ነች
የአረብ ኢምሬትስ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ በአሜሪካ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።
የዱባይ ምክትል ገዥና የአረብ ኢምሬትስ ብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሼክ ታህኑን ቢን ዛይድ አልናህያን በነገው እለት በአሜሪካ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ሊያደርጉ ነው።
ሼክ ሼክ ታህኑን ቢን ዛይድ በኃይትሀውስ ከተለያዩ የአሜሪካ ባለስልጣናት ጋር እንደሚወያዩ ይጠይቃል። ስብሰባው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚና የቴክኖሎጂ ግንኙነት በማጠናከር ላይ እንደሚያተኩር ዋም ዘግቧል።
ከዚህ በተጨማሪም ውይይቱ በቀጣናው ባሉ አሁናዊ ችግሮችና ለአስርት አመታት የቆመውን የአሜሪካ-አረብ ኢምሬትስ ስትራቴጂካዊ ትብብር የማጠናከር ጉዳይም አጀንዳ ይሆናል ተብሏል።
አረብ ኢምሬትስ የአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ ስትራቴጂካዊ አጋር ነች።