ስፖርት
ለመጀመሪያ ጊዜ ማራቶን ውድድሩን ያካሄደው አትሌት አበጀ አያና የፓሪስ ማራቶን አሸናፊ ሆነ
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የፓሪስ ማራቶን በበላይነት አጠናቀቁ
በሴቶች በተካሄደ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል
በዛሬው እለት በተካሄደው የ2023 የፓሪስ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በበላይነት ማጠናቀቅ ችለዋል።
በወንዶች በተካሄደው የማራቶን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በማራቶን ውድድር የተሳተፈው አትሌት አበጀ አያና አሸናፊ በመሆን ማጠናቀቅ ችሏል።
- በማራቶን ታሪክ 2ኛው ፈጣኑ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በዘንድሮው የለንደን ማራቶን ይጠበቃል
- ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ በመያዝ የፓሪስ ማራቶንን አሸነፉ
አትሌት አበጀ አያና የመጀመሪያው የሆነውን የማራቶን ውድድሩን 2 ሰዓት ከ07 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመግባት ማሸነፍ ችሏል።
ውድድሩን ለረጅም ሰዓት ሲመራ የነበረው ሌላኛው ኢትዮጵያውው አትሌት ጉዮ አዶላ 2ኛ ደረጃ በመያዝ ርቀቱን ሲያጠናቀቅ ኬንያዊው አትሌት ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችሏል።
ከፍተኛ ፉክክር በታየበት የሴቶች ማራቶን ኬንያዊቷ አትሌት ሄላ ኪፐሮፕ ውድድሩን በበላይት ስታጠናቅቅ ኢትዮጵያውያኑ አትሌት እና አታለል አንሙት አትሌት ፍቅርተ ወረታ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።