ስፖርት
የ17 ዓመቱ አትሌት አብዲሳ ፈይሳ የካርልስሩሄ ቤት ውስጥ አትሌቲክስ ውድድር 3000 ሜትር አሸናፊ ሆነ
አትሌት አብዲሳ ፈይሳ በ17 ዓመቱ በርቀቱ ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበ በእድሜ ትንሹ አትሌት መሆን ችሏል
በ3000 ሜትር በሴቶቸ በተካሄደ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 5ኛ ተከታትለው በመገባት አሸንፈዋል
በጀርመን ካርልስሩሄ ትናንት ምሽት በተካሄደ የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ3000 ሜትር በሁለቱም ጾታዎች ማሸነፍ ችለዋል።
በወንዶች በተካሄደው ውድድር የ17 ዓመቱ አትሌት አብዲሳ ፈይሳ የካርልስሩሄ ቤት ውስጥ 3000 ሜትር አሸናፊ መሆን ችሏል።
አትሌት አብዲሳ ፈይሳ በመጀመሪያው የቤት ውስጥ ውድድሩ ርቀቱን 7:40.35 በሆነ ሰዓት የጨረሰ ሲሆን፤ በ17 ዓመቱ በርቀቱ ፈጣን ሰዓት ያስመዘገበ አትሌት መሆን መቻሉን ዓለምአቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በርቀቱ ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት አዲሱ ግርማ 7:41.53 በሆነ ሰዓት በመግባት 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል።
በበ3000 ሜትር በሴቶች በተካሄደው ውድድውርም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 5ኛ ተከታትለው በመገባት ማሸነፋቸው ተነግሯ።
አትሌት ለምለም ኃይሉ 8:37.55, በሆነ ሰዓት ርቀቱን በአንደኝነት ስታጠናቅቅ፣ አትሌት ወርዉኃ ጌታቸው 2ኛ፣ አትሌት ዳዊት ስዩም 3ኛ፣ አትሌት ሚዛን አለም 4ኛ እንዲሁም አትሌት ዘርፌ ወንድማገኝ 5ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።