በአውሮፓ በተከሰቱ የመብረቅ አደጋዎች የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ
ጣልያን ፈረንሳይ እና አውስትራልያ የመብረቅ አደጋዎች የተከሰቱባቸው ሀገራት ናቸው
አውሮፓ በድርቅ የተጠቃች ሲሆን አሁን ደግሞ ከባድ ዝናብ በመዝነብ ላይ ይገኛል
በአውሮፓ በተከሰቱ የመብረቅ አደጋዎች የ12 ሰዎች ህይወት አለፈ።
በደቡባዊ የአውሮፓ ሀገራት ያጋጠሙ ከፍተኛ ሙቀትን ተከትሎ በጣልያን፣ ፈረንሳይ፣ ስፔን፣ ፖርቹጋል እና ግሪክ የእሳት አደጋ ጉዳት አስከትሏል።
ይህ ሙቀት ተባብሶ ወደ መሀል አውሮፓ ተስፋፍቶ እንግሊዝ እና ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ድርቁ ባስከተለው ከፍተኛ ሙቀት በየቦታው የእሳት አደጋዎች ፈተና ሆነው ቆይተውም ነበር።
የሰደድ እሳት አደጋዎችን ለመቆጣጠር እልህ አስጨራሽ ትግል ሲያደርጉ የከረሙት አውሮፓውያን አሁን ደግሞ በከባድ ዝናብ መፈተን ጀምረዋል።
በፈረንሳይ ፣ አውስትራሊያ እና ጣልያን በደረሱ ከባድ ዝናብ ምክንያት 12 ሰዎች መሞታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
በማዕከላዊ እና ደቡባዊ የአውሮፓ ሀገራት በደረሱ የመብረቅ አደጋዎች ከሞቱት 12 ሰዎች ውስጥ ሶስቱ ህጻናት እንደሆኑም ተገልጿል።ከሟቾቹ በተጨማሪም 13 ሰዎች ደግሞ የተጎዱ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ አምስቱ ህጻናት ናቸው ተብሏል።
ከሟቾች ውስጥ አራቱ ከባድ ዝናብን ተከትሎ ዛፎች ወድቀው በሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሱም ተጠቅሷል።ከዝናቡ በተጨማሪም ከባድ ንፋስ መኖሪያ ቤቶችን እና መዝናኛ ስፍራዎችን በማውደም ላይ ይገኛልም ተብሏል።