የመብረቅ አደጋው ሙሽራውና አጃቢዎቹ ሙሽሪትን ለመውሰድ በሄዱበት ወቅት ነው ያጋጠማቸው
በባንግለዴሽ በደረሰ የመብረቅ አደጋ በአንድ ሰርግ ላይ የበሩ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለጸ።
እንደ አካባቢው ባለስልጣናት ገለጻ ሙሽራውን ጨምሮ 14 ሰዎች ላይም በመብረቅ አደጋው ጉዳት መድረሱን የሮይተርስ ዘገባ ያመለክታል።
የመብረቅ አደጋው የደረሰው የሙሽራው እና አጃቢዎች ሙሽሪትን ለመውሰድ በሄዱበት ወንዝ ዳር በምትገኝ ሺብጃኒ ከተማ ከጀልባ ላይ በመውረድ ላይ እያሉ ነው።
እንደ አካባው ሰዎች ገለጻ ሙሽራው እና አጃቢዎቹ ከጀልባው ላይ በሚወርዱበት ጊዜ በበርካታ መብረቆች መመታቸውን ተናግረዋል።
በደቡብ ኢሲያ የዓመቱ በመቶዎች የሚቆተሩ ሰዎች በመብረቅ አደጋ ህይወታቸው እንደሚያልፍ ከስፍራው ተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2016 በአንድ ወር ብቻ በባንግላዴሽ በደረሱ የመብረቅ አደጋዎች ከ200 በላይ ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ ከእነዚህም ውስጥ የ82 ሰዎች ሕይወት በአንድ ቀን ውስጥ ነው ያለፈው።
በዚህ ጊዜም ሀገሪቱ መብረቅን እንደ ብሄራዊ የተፈጥሮ አደጋ አውጃ እንደበረ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የመብረቅ አደጋዎች መበራከት መንስኤው የደኖች መመናመን እንደሆነ የሚናገሩት የዘርፉ ባለሙያዎች፤ ከዚህ ቀደም መብረቅን ቀድመው ይከላከሉ የነበሩ ረጃጅም ዛፎች በመቆረጣቸው ነው አደጋው የተበራከተው ሲሉም ያነሳሉ።