ፖለቲካ
በዘንድሮው ምርጫ 125 እጩዎች በግል ለመወዳደር ተመዝግበዋል- ምርጫ ቦርድ
ምርጫ ምልከት ከወሰዱ 49 ፓርቲዎች ውስጥ 47 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን አስመዝግበዋል
ኦነግ እና ኦፌኮ ቦርዱ ባስቀመጠው በቀነገደቡ እጩዎቻቸውን ማስመዝገብ አልቻሉም
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የእጩዎች ምዝገባ መጠናቀቅን አስመልክቶ በዛሬው እለት መገለጫ ሰጥቷል።
ቦርዱ በመግለጫውም ሁሉም ህጋዊ ሰውነት ያላቸው ፓርቲዎች በራሳቸው ወይም በፈጠሩት ትብብር/ህብረት አማካኝነት 53 የፖለቲካ ፓርቲዎች 49 ምርጫ መወዳደሪያ ምልክት መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።
ምርጫ ምልክት ከወሰዱ 49 ፓርቲዎች ውስጥ 47 ፓርቲዎች እጩዎቻቸውን ማስመዝገባቸውንም ቦርዱ በመግለጫው አስታውቋል። 47ቱ ፓርቲዎች በአጠቃላይ 8209 እጩዎች አስመዝግበዋከል፡፡
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እጩዎቻቸውን ያላስመዘገቡ ፓርቲዎች መሆናቸውም ታውቋል።
ዘንድሮው ምርጫ 125 እጩዎች በግል ለመወዳደር ተመዝግበዋል፡፡
ቦርዱ በመግለጫው አክሎም በእጩ ምዝገባ ወቅት ችግሮች አጋጥመውት እንደነበረም ያነሳ ሲሆን፤ በተለይም ከ16 በላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች አቤቱታዎችን አቅርበው መፍትሄ እንደሰጣቸው ገልጿል።
ምርጫ 2013 በመጭው ግንቦት 28 እንደሚካሄድ ምርጫ ቦርድ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡