ሀገሪቱን እየመራ ያለው ፓርቲ ከምክር ቤቱ አጠቃላይ 255 መቀመጫዎች ውስጥ 58 በመቶውን አሸንፏል
ሀገሪቱን በማስተዳደር ላይ ያለው ፓርቲ ከምክር ቤቱ አጠቃላይ 255 መቀመጫዎች ውስጥ 58 በመቶዎቹን እንዳሸነፈ ሲጂቲኤን አፍሪካ አስነብቧል።
የምርጫው ውጤት ሀገሪቱን በማስተዳደር ላይ ላሉት ፕሬዘዳንት አላሳን ኦታራ ማሳካት ለሚፈልጉት የፖለቲካ አጀንዳ ትልቅ እድል እንደሆነ ዘገባው ጠቁሟል።
ፕሬዘዳንት አታራ በምርጫው ተዋህደው እንደ አንድ ተቋም ከተወዳደሩት የቀድሞው ፕሬዘዳንት ሎረን ባግቦ እና ካኖን በዴ ውህድ ፓርቲ ከባድ ፈተና ቢገጥማቸውም ምርጫውን ማሸነፋቸው ተገልጿል።
ፕሬዘዳንት ኦታራ የአሁኑን ምርጫ ሲያሸንፉ ለሶስተኛ ጊዜ ሲሆን በዓለማችን ቀዳሚ የካክዋ አምራጭ ሀገራቸውን የበለጠ ተጠቃሚ እንድትሆን ማድረግ ቀዳሚ ስራቸው እንደሚሆን ተናግረዋል።
ከአንድ ወር በፊት በተደረገው በዚህ ምርጫ በሀገሪቱ ብተከሰተው ሁከት የ85 ሰዎች ህይወት ማለፉ አይዘነጋም።