ልዩልዩ
በአፍሪካ እስካሁን ከ13 ሚሊየን በላይ ሰዎች የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባት ወስደዋል
ሞሮኮ፣ ናይጄሪያ እና ጋና ዜጎቻቸውን በብዛት የከተቡ ሀገራት ናቸው
የአፍሪካ ሀገራት እስካሁን 34 ነጥብ 6 ሚሊየን ክትባቶችን ተቀብለዋል
በአፍሪካ እስካሁን ከ13 ሚሊየን ዶዝ በላይ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባቶች በአግባቡ ለሰዎች መሰጠታቸውን የአፍሪካ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (አፍሪካ ሲ.ዲ.ሲ) አስታወቀ።
አፍሪካ ሲ.ዲ.ሲ በትናንትናው እለት ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫ ፣ እስከ ያዝነው ሳምንት ድረስ ብቻ በአፍሪካ 13 ነጥብ 9 ሚሊየን ዶዝ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባቶች በአግባቡ ለሰዎች ተሰጥተዋል ብሏል።
ከእነዚህም ውስጥ ሞሮኮ 8 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶዝ፣ ናይጄሪያ 1 ሚሊየን ዶዝ፣ ጋና 681 ሺህ 211 ዶዝ ክትባት ለዜጎቻቸው በመስጠት ከአህጉሪቱ በርካታ ዜጎችን የከተቡ ሀገራት ሆነዋል።
አፍሪካ ሲ.ዲ.ሲ በሪፖርቱ አክሎም ፣ የአፍሪካ ሀገራት እስካሁን 34 ነጥብ 6 ሚሊየን ክትባቶችን በተለያየ መልኩ መቀበላቸውን አስታውቋል።
በዚህም መሰረት 32 የአፍሪካ ሀገራት ክትባቱን በኮቫክስ ጥምረት እንዲሁም ከጥምረቱ ውጪ ከ12 ተጨማሪ ሀገራት ማግኘታቸውን ነው ሪፖርቱ ያመለከተው።