እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው ጥቃት 13ሺ ህጻናት መገደላቸውን ዩኒሴፍ አስታወቀ
ኤጀንሲው እንደገለጸው ግድያ ከተፈጸመባቸው በተጨማሪ በርካታ ህጻናት በረሀብ እየተሰቃዩ ይገኛሉ
በጋዛ እየተባባሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስ መፍትሄ እንዲያገኝ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ በእስራኤል ላይ ጫና እያደረገ ነው
እስራኤል በጋዛ በፈጸመችው ጥቃት 13ሺ ህጻናት መገደላቸውን ዩኒሴፍ አስታወቀ።
የተባበሩት መንግስት ድርጅት(ተመድ) የህጻናት ኤጀንሲ እስራኤል በጋዛ እየፈጸመችው ባለው ጥቃት 13ሺ ህጻናት መገደላቸውን አስታውቋል።
ኤጀንሲው እንደገለጸው ግድያ ከተፈጸመባቸው በተጨማሪ በርካታ ህጻናት በረሀብ እየተሰቃዩ ይገኛሉ።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ካትሪን ሩዜል "በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናት ጉዳት ደርሶባቸዋል ወይም የት እንዳሉ ለማወቅ አልቻልንም። በፍርስራሽ ውስጥ ተቀብረው ሊሆንም ይችላል...ይህን ያህል የህጻናት የሞት ቁጥር በሌሎች ሀገራት ባሉ ግጭቶች አልታየም" ሲሉ መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
ዳይሬክተሯ በከፍተኛ የምግብ እጥረት ሲሰቃዩ የነበሩ ህጻናት ማየታቸውን የገለጹት ሩዜል ዓለም ግን ድምጽ እያሰማ አይደለም ብለዋል።
ዳሬክተሯ እርዳታ የጫነ ተሽከርካሪ ወደ ጋዛ ለማስገባት ከፍተኛ እንቅፋት እያጋጠማቸው እንደሆነ ተናግረዋል።
በጋዛ እየተባባሰ ያለው ሰብአዊ ቀውስ መፍትሄ እንዲያገኝ ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ በእስራኤል ላይ ጫና እያደረገ ነው።
አንድ የተመድ ባለሙያ በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ እስራኤል ከፍተኛ ረሀብ እንዲፈጠር የጋዛን የምግብ አቅርቦት ስርአታት እንዲዛባ አድርጋለች የሚል ሪፖርት አቅርበው ነበር።ነገርግን እስራኤል ይህን ክስ ውድቅ አድርጋዋለች።
እስራኤል እየፈጸመች ባለው ሰፊ ጥቃት አብዛኛው የጋዛ ህዝብ መፈናቀሉን እና 30ሺ ሰዎች መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
እሰራእል በጋዛ የዘርማጥፋት መጽማለች የሚል ክስ በአለምአቀፉ ፍርድ ቤት ቀርቦባታል። ነገርግን እስራኤል የቀረበባትን ክስ ውድቅ አድርጋዋለች።
በጋዛ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥረቶች እየተደጉ ባለበት ወቅት እስራኤል በግብጹ ድንበር የምትገኘውን ራፋ ከተማን ለማጥቃት የያዘችውን እቅድ አጽድቃዋለች።