ፕሬዝዳት ጆ ባይደን “ኔታንያሁ እስራኤልን እየጎዳ ነው” አሉ
ፕሬዝዳንት ባይደን እስራኤል በጋዛ ጦርነት “ልታጥሳቸው የማይገባ ቀይ መስመሮች አሉ” ብለዋል
ባይደን እስራኤል ራፋህን መውረር ለጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ “ቀይ መስመር” ነው ብለዋል
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የጋዛ ጦርነትን አየመሩበት ያለው መንግድ እስራኤልን ከመጥቀም ይልቅ እየጎዳ ነው ሲሉ አሳሰቡ።
ባይደን ከኤም.ኤስ.ኤን.ቢ.ሲ ጋር በዳረጉት አነጋጋሪ ቃለ መጠይቅ፤ እስራኤል በጋዛ ጦርነት “ልትጥሳቸው የማይገባ ቀይ መስመሮች አሉ” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያን ኔታንያሁ የጋዛ ጦርነትን አየመሩበት ያለው መንግድ እስራኤልን ከመጥቀም ይልቅ እየጎዳ ነው ያሉት ፕሬዝዳት ባይደን፤ “ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በጋዛ ለሚጠፋው ንፁሀን ህይወት የበለጠ ትኩረት መስጠት አለባት” ብለዋል።
- ደቡብ አፍሪካ ዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት በእስራኤል ላይ ተጨማሪ እርምጃ እንዲወስድ ጠየቀች
- የአለም ምግብ ፕሮግራም እስራኤል በጋዛ እርዳታ እንዳላቀርብ ከልክላኛለች አለ
እስራኤል በጋዛ የሚገኘውን ሃማስ ለማጥፋት የያዘችውን አቋም እንደሚደግፉ ያስታወቁት ፕሬዘዳን ባይደን፤ ነገር ግን በንጹኃን ዜጎች ላይ ከሚደርሰው እልቂት እና ወደ ጋዘ እርዳታ እንዳይገባ ከሚደረገው ክልከላ ጋር ተያይዞ በአስተዳደራቸው እና በጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ መካከል ያሉ አለመግባባቶች እየሰፉ መጥተዋል ነው የተባለው።
ባይደን እስራኤል ራፋህን መውረር ለጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ “ቀይ መስመር” ነው ሲሉም ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አሳስበዋል ነው የተባለው።
የባይደን አስተዳደር እሰራኤል በራሃፍ የተጠለሉ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ዜጎች ደህንነታቸው ተጠብቆ ስፍራዉን ሳይለቁ የታቀደ ጥቃት እንዳትጀምር ሲያሳስብ መቆየቱም ይታወሳል።
ባሳለፍነው ሃሙስ ባይደን አሜሪካ ለጋዛ የእርዳታ እህሎችን በባህር ለማድረስ ይቻል ዘንድ ጊዜያው ወደብ እንደምትገነባ ማስታወቃቸው ይታወሳል።
ባይደን ባለፈው ወር እስራኤል እና ሃማስ በረመዳን ወቅት በጊዜያዊ ውጊያን ለማቆም ሊስማሙ እንደሚችሉ ተስፋ እንዳላቸው ገልጸው ነበር።
ሆኖም ግን ሃማስ እና እስራኤልም ለማሸማገል ባሳለፍነው ሳምንት በግብጽ ካይሮ ሲደረግ የነበረው ውይይት ያለ ውጤት መጣቀቁ ይታወሳል።