
ዲጄ ዳንኤል በትናንትናው ዕለት በይፋ መታወቂያ ተሰጥቶት ስራ ጀምሯል
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ያሞካሹት የ13 ዓመቱ የካንሰር ታማሚ ማን ነው?
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትናንትናው ዕለት በሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት ተገኝተው ንግግር አድርገዋል፡፡
በንግግራቸው ላይ ከተሰሙ ጉዳዮች መካከል ዲጄ ዳንኤል የተሰኘው ታዳጊ ሲሆን ታዳጊውን አሞካሽተዋል፡፡
ዲጄ ዳንኤል ከስድስት ዓመት በፊት በጭንቅላት ካንሰር መጠቃቱን እና ከአምስት ወር በላይ መኖር እንደማይችል በሐኪሞቹ ይነገረዋል፡፡
ሕክምናውን ሲከታተል የቆየው ይህ ህጻን አሁን ላይ የ13 ዓመት ታዳጊ የሆነ ሲሆን ከልጅነቱ ጀምሮ ፖሊስ የመሆን ምኞት እንደነበረው ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ከካንሰር ህመሙ ማገገሙ የተገለጸው ይህ ታዳጊ የልጅነት ህልሙ እንዲሳካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ረድተውታል ተብሏል፡፡
ዲጄ ዳንኤል ከአባቱ ጋር ሆኖ በምክር ቤቱ የተገኘ ሲሆን በይፋ የአሜሪካ ሚስጢራዊ ፖሊስ አባል እንዲሆን መደረጉን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ንግግር እያደረጉ እያለ የሀገሪቱ ሚስጢራዊ ፖሊስ ሀላፊ የሆኑት ሲን ኩራን የስራ መታወቂያውን ለዲጄ ዳንኤል አስረክበውታል፡፡
የምክር ቤት አባላቱ ጭብጨባ ያሰሙ ሲሆን ታዳጊው በደስታ ሲስቅ እና አባቱን በመገረም ሲመለከት የነበረው ድባብ ብዙዎችን አስደስቷል፡፡