በትራፊክ ፖሊስ መኪና ላይ ጂፒኤስ የገጠመችው ባለ ታክሲ
ግለሰቧ በከተማዋ ባሉ ስድስት የትራፊክ ፖሊስ መኪኖች ላይ የእንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ ገጥማ ተገኝታለች

የትራፊክ ፖሊሶቹ መኪናቸውን ለጥገና በላኩበት ወቅት ነበር የማያውቁት መቆጣጠሪያ መገጠሙን ያወቁት
በትራፊክ ፖሊስ መኪና ላይ ጂፒኤስ የገጠመችው ባለ ታክሲ
ዙ የተሰኘችው ቻይናዊት በሁቤ ግዛት ሺያንግያንግ ከተማ የምትኖር ሴት ናት።
የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች ያሏት ይህች ሴትም ትራፊክ ፖሊሶቹ ያሉበትን ብታውቅ የተሻለ ገቢ ልታገኝ እንደምትችል ታስባለች።
በዚች ከተማም ስድስት ትራፊኮች ፖሊሶች የከተማዋን ትራንስፖርት እንቅስቃሴ የሚከታተሉበት የየራሳቸው አምቡላንስ አላቸው።
ትራፊኮቹ በነዚህ አምቡላንሶች እንደሚንቀሳቀሱ የተረዳችው ይህች ባለ ታክሲም እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ ወይም ጂፒኤስ በድምብቅ እንዲገጠምላቸው ታደርጋለች።
ባለታክሲዋም መኖሪያ ቤቷ ሆና የታክሲ ፎፌሮቿን በዚህ ግቡ፣ ትራፊክ ፖሊሶች እየመጡ ነው እና መሰል መረጃዎችን ስትሰጥ ቆይታለች ተብሏል።
በመጨረሻም አንዱ ትራፊክ ፖሊስ መኪናው ብልሽት ማሳየቷን ተከትሎ ወደ ጥገና ቦታ ሲወስድ የማያውቀው ጂፒኤስ እንደተገጠመለት ያስተውላል።
ጉዳዩን ለተቋሙ ያሳወቀው ይህ ፖሊስ ጂፒኤሱ በፖሊስ እንዳልተገጠመ ይነገረዋል።
ቆይቶ በተደረገ ምርመራም በከተማዋ ያሉ የትራፊክ ፖሊስ መኪኖች ሁሉ በማያውቁት መልኩ ጂፒኤስ እንደተገጠመላቸው ይረጋገጣል።
ፖሊስ ባደረገው ምርመራም በከተማዋ የምትኖር አንድ ባለታክሲ ሴት እንደፈጸመችው ተረጋግጧል።
ባለ ታክሲዋ ጂፒኤሱን በትራፊክ ፖሊስ መኪኖች ላይ ከመቼ ጀምሮ እንደገጠመችው በግልጽ ያልተገለጸ ሲሆን ግዥውን ከፈጸመችው ግን አንድ ዓመት እንደሆናት ቻይና ዴይሊ ዘግቧል።
ፖሊስ ይህን ወንጀል በፈጸመችው ባለ ታክሲ ላይ የስምንት ቀናት ጉልበት ስራ እና የ500 ዩዋን ወይም 70 ዶላር ቅጣት ጥሎባታል ተብሏል።