ከፎቅ ለመውረድ በተፈጠረ መገፋፋት 14 ኬንያውያን ህጻናት ተማሪዎች ሞቱ
ከፎቅ ለመውረድ በተፈጠረ መገፋፋት 14 ኬንያውያን ህጻናት ተማሪዎች ሞቱ
በምእራባዊ ኬንያ ተማሪዎች የትምህርት ክፍለ ጊዜያቸውን ጨርሰው ከፎቅ ወደ መሬት ሲወርዱ በተፈጠረ መጨናነቅ ምክንያት የ14 ተማሪዎችህይወትማለፉን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
ሮይተርስ የምእራብ ሪጅንን የፖሊስ አዛዥ ፐሪስ ኪማኒን ጠቅሶ እንደዘገበው ሌሎች 39 ተማሪዎች ካካሜጋ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት መጎዳታቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡
“14 ልጆችን አጥተናል” በማለት የትምህርት ሚኒስትሩ ለሲቲዝን ቲቪ ተናግረዋል፡፡አንድ “የጠፋ ህይወት የብዙ ሰው ህይወት ነው፡፡”
የዳይሊ ኜሽን ጋዜጣ እንደዘገበው ጥቂቶቹ ተማሪዎች በሚሮጡት ወቅት ከሦስተኛ ፎቅ መውቃቸውን ዘግቧል፡፡
የኬንያ ቀይመስቀል ቃል አቀባይ ፒተር አብዎ ተማሪዎቹ ከፎቅ ወደ መሬት በሚወርዱበት ጊዜ በደረጋው ላይ መገፋፋት ነበር ብለዋል፡፡