በደስታና ሀዘን የታጀበው የብሪታኒያ ከህብረቱ መውጣት
በደስታና ሀዘን የታጀበው የብሪታኒያ ከህብረቱ መውጣት
የብሪታኒያ ከአውሮፓ ህብረት መውጣት ወይንም “ብሬኤግዚት” ከህብረቱ የመውጣት ህዝበውሳኔ ከተካሄደ ከሶስት አመታት በኋላ እውን ሆኗል፡፡
ከ47 አመታት የአውሮፓ ህብረት የአባልነት ቆይታ በኋላ ብሪታኒያ ህብረቱን ለቃ መውጣቷን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ሀገሪቱ ከህብረቱ ለመውጣት ህዝበውሳኔ ካካሄደች በኋላ ከህብረቱ ለመውጣት ያደረገችው ጥረት ለሶስት አመታት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡
ይህ ታሪካዊ ክስተት በብሪታኒያ በደስታትና በታቃውሞ የታጀበ ሆኖ አልፏል፡፡
በሀዘን የተዋጡት የስኮትላንድ ነዋሪዎች ሻማ በማብራት ሀዘናቸውን ሲገልጹ፣ በተቃራኒው ደግሞ የብሪታኒያን ከህብረቱ መውጣት የሚደግፉ በለንደን ፓርላማ አደባባይ ደስታቸውን ገልጸዋል፡፡
የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሀገሪቱን በአንድነት ወደፊት እንደሚመሯት ቃል ገብተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብሪታኒያ ከህብረቱ ከመውጣቷ አንድ ሰአት በፊት በማህበራዊ ሚዲያ ባስተላለፉት መልእክት ”ይሄ ለብዙ ህዝብ ደስታን የሚፈጥርና ይሆናል ብለው የማያስቡት ክስተት ነው” ብለዋል፡፡
በርግጥ በክሰተቱ የተረበሹና የከሰሩ መኖራቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ገልጸዋል፡፡
እንደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገላጻ ብሪታኒያ ከህብረቱ ለመውጣት ያደረገችው ትንቅንቅና የፖለቲካው ውጣውረድ በቀላሉ አያልቅም ብለው ሲሰጉ የነበሩ ሶስተኛ ቡድኖች፣ ምናልባትም ትልቅ ቁጥር ያላቸው ዜጎችም ነበሩ፡፡
ብሪታኒያ ከህብረቱ ለመውጣት ስትወስን ህብረቱ ለሀገሪቱ በማይመችበት ደረጃ ላይ በመድረሱ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡