አብን “በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋ ወንጀል” እየተፈጸመ መሆኑን ገልጿል
አብን “በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋ ወንጀል” እየተፈጸመ መሆኑን ገልጿል
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ብሔራዊ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በሀገሪተ በተለያዩ አካባቢዎች የተደረጉ ግድያዎችን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲካሄድ መወሰኑን አስታወቀ፡፡
ንቅናቄው በአማራ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋ ወንጀል እየተፈጸመ እንደሆነም ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስፍሯል፡፡ “በሀገሪቱ በአማራዎች ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል ተፈጽሟል“ ያለው አብን ይህንን የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ በአዲስ አበባና በአማራ ክልል ከተሞች እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ሰላማዊ ሰልፉ በዋናነት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በአማራዎች ላይ እየደረሰ የሚገኘውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እና ሌሎች መዋቅራዊ እንዲሁም ሕግ ሰራሽ መገለሎችን የሚያወግዝ እንደሆነ ገልጿል፡፡
በዚህም መሰረት በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች ጥቅምት 18 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲሁም በአዲስ አበባ ዕሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2013 ዓ.ም እንዲደረግ ውሳኔ ማሳለፉን በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አስታውቋል።
አብን እያካሄደ እንደሆነ በገለጸው አስቸኳይ ስብሰባ የአማራን ሕዝብ እየገጠሙት ባሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየተወያየ መሆኑን ገልጿል፡፡