የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ የአሜሪካን አምባሳደር ጠርተው ማብራሪያ ጠየቁ
በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ጦርነት መቀስቀስ ተቀባይነት የለውም ብለዋል አቶ ገዱ
ፕሬዘዳንት ትራምፕ ኢትዮጵያ የግድቡን ስምምነት ጥሳለች፤ ግብጽ “ግድቡን ያፈነዳዋለች” የሚል ንግግር አሰምተው ነበር
ፕሬዘዳንት ትራምፕ ኢትዮጵያ የግድቡን ስምምነት ጥሳለች፤ ግብጽ “ግድቡን ያፈነዳዋለች” የሚል ንግግር አሰምተው ነበር
የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው የአሜሪካ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ ስለግድቡ በሰጡት አስተያየት ዙሪያ ማብራሪያ ለመጠየቅ በኢትየጵያ የአሜሪካን አምባሳደር ጠሩ፡፡
የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትናንትናው እለት ከሱዳንና ከእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር በነበራቸው የስልክ ንግግር ወቅት ኢትዮጵያ የግድቡን ስምምነት ጥሳለች፤ ለግብጽ በዚህ ሁኔታ መቀጠል አስቸጋሪ ስለሆነ “ግድቡን ያፈነዳዋለች” የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር፡፡
ሚኒስትሩ ትራምፕ በስልክ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ስለግድቡ የሰጡትን በሚመለከር ማብራሪያ ለመጠየቅ ነው አምባሳደር ማይክ ራይኖርን የጠሩት፡፡
አቶ ገዱ በግድቡ ላይ የተሰጠው አስተያየት አሳሳችና ተገቢ ያልሆነ ነው ምክንያቱም ግድቡ የውሃውን መፍስስ ስለማያቆመው፡፡
ስልጣን ላይ ባለ የአሜሪካ ፕሬዘዳንት፤ በኢትዮጵያ በግብጽ መካከል ጦርነት መቀስቀስ የቆየውን ግንኙነትም ሆነ ስትራቴጂክ ጥምረት አያንጸባርቅም፤በአለምአቀፍ ህግም ተቀባይነት የለውም ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡
ሚኒስትር ገዱ ኢትዮጵያ በሉአላዊነቷ ላይ ለሚሰነዘሩ ጥቃቶች አንትነረተከክም፤ ድርድሩንም በአፍሪካ ህብረት በተቀመጠው ማእቀፍ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባችው ያለው ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ተገንብቶ ከመጠናቀቅ የሚያግደው ኃይል አለመኖሩን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ዛሬ ጠዋት ባወጣው በመግለጫው ገልጿል፡፡