ጥቃቶቹ እየተባባሱ መምጣታቸውን የገለጸው ቴዲ የመንግስት አካል ድጋሚ እንዳይፈጸሙ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቋል
ጥቃቶቹ እየተባባሱ መምጣታቸውን የገለጸው ቴዲ የመንግስት አካል ድጋሚ እንዳይፈጸሙ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቋል
ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ ወይንም ቴዎድሮስ ካሳሁን በኢትዮጵያ የተለያዩ ክፍሎች እየተካሄዱ ያሉት የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ማንነትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች መባባሳቸው እንደሚሳስበው በፌስቡክ ገጹ ጽፏል፡፡
ጥቃቶቹ የማያባሩና እየተባበሱ መምጣታቸውን የገለጸው ቴዲ አፍሮ ይህን እየተባባሰ የመጣውን ጥቃት የሚመለከተው የመንግስት አካል ለማስቆም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቋል፡፡
ቴዲ አፍሮ “የዜጎችን ሰላምና ደህንነት በዋናነት መጠበቅ ያለበት” መንግስት ጥቃቶች እንዳይፈጸሙ ቅድመ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በደቡብ ክልል መንግስት “ለውጥ”የማደናቀፍ አላማ አላቸው ባላቸው አካላት ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፤ተፈቅለዋል፡፡
ከሳምንት በፊት በደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን በተፈጸመ ጥቃት 31 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ይህን ተከትሎም በጥቃቱ እጃቸው አለበት የተባሉ ከ50 በላይ ሰዎች መያዛቸውን የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽንም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈጸመውን ተደጋጋሚ ግድያና የጽምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን ሞት ተከትሎ በተለይ በኦሮሚያ ክልል የተፈጸመውን ማውገዙ ይታወሳል፤ጥቃት እንደሚያሳስበውም በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል፡፡