ከሰሃራ በታች ዝቅተኛ ኢንተርኔት ዋጋ የሚያስከፍሉ ሀገራት የትኞቹ ናቸውʔ
ጋና ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት በዝቅተኛ ዋጋ ቀዳሚ ስትሆን ከዓለም 40ኛ ላይ ተቀምጣለች
ኢትዮያጵያ ጨምሮ፤ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና ኬንያ በዝርዝሩ ተካተዋል
አለም አቀፍ የሞባይል ዳታ ዋጋ ላይ የተደረገ ጥናት በፈረንጆቹ በ2022 በጣም ርካሹን እና በጣም ውድ የሆነውን የሞባይል ዳታ የሚያቀርቡ ሀገራት ዝርዝር ይፋ አድርጓል።
በብሪታኒያው “Cable.co.uk” የተሰራው ጥናት 233 ሀገራት ያለውን 5,292 የሞባይል ዳታ ጥቅል ዋጋ መረጃ በመተንተን የተሰራ ሲሆን፤ ሪፖርቱ በሁሉም ሀገራት የ1 ጊጋ ባይት (1GB) የሞባይል ዳታ ዋጋን ተመልክቷል።
ከሪፖርቱ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ከሰሃራ በታች ያሉ የአፍሪካ ሀገራት በአጠቃላይ ለሞባይል ዳታ ዋጋ በውድነቱ ከአለም ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።
ሆኖም ግን 5 ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ኢንተርኔትን በርካሽ ዋጋ ከሚያቅርቡ 50 የዓለም ሀገራ ውስጥ መካተት መቻላቸው ተመላክቷለል።
ከእነዚህም ውስጥ ጋና ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት ኢንተርኔትን በርካሽ ዋጋ በማቅረብ ቀዳሚ ሆናለች።
ኢንተርኔትን በርካሽ ዋጋ የሚያቀርቡ 5 ከሰሃራ በታች ያሉ ሀገራት
1. ጋና 1 ጊጋ ባይት የኢንትርኔት ዳታ በ0.61 ዶላር
2. ሶማሊያ 1 ጊጋ ባይት ኢንትርኔት ዳታ በ0.63 ዶላር
3. ናይጄሪያ 1 ጊጋ ባይት ኢንትርኔት ዳታ በ0.71 ዶላር
4. ታንዛኒያ 1 ጊጋ ባይት ኢንትርኔት ዳታ በ0.71 ዶላር
5. ሱዳን 1 ጊጋ ባይት ኢንትርኔት ዳታ በ0.75 ዶላር
ኢትዮጵያ በዝርዝሩ ውስጥ የተካተተች ሲሆን፤ ደረጃዋም ከሰሃራ በታች ካሉ ሀገራት መካከል ኢንተርኔትን በዝቅተኛ ዋጋ በማቅረብ 10ኛ ከዓለም ደግሞ 73ኛ ላይ ተቀምጣለች።
በጥናቱ መሰረት በኢትዮጵያ የ 1 ጊጋ ባይት የኢትነርኔት ዳታ ዋጋ 1 የአሜሪካ ዶላር ወይም 52 ብር ገደማ እንደሆነ ተመላክቷል።
በጥናቱ ኢንተርኔትን በርካሽ ዋጋ በማቅረብ እስራኤል ከዓለም ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን፤ 1 ጊጋ ባይት ኢንትርኔት በ0.04 ዶላር ማግኘት ይቻላል።
በደቡብ አትላንቲክ ባር ላይ የምትገኘው ሴንት ሄሊና ደሴት ደግሞ ከፍተኛ የኢንተርኔት ዋጋ በማስከፈል የሚወዳደራት የለም ተብሏል፤ በሀገሪቱ 1 ጊጋ ባይት ኢንተርኔት ከፈለግን 41.06 የአሜሪካ ዶላር መክፈል የግድ ይለናል።