በስፔን ካናሪ ደሴት የ17 ስደተኞች ህይወት አለፈ
በጀልባዋ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ሁሉም ስደተኞች ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ነው የተነሱት
ከአደጋው የተረፉ 3 ሰዎች በስፔን ጦር ሄሊኮፕተር ቴንሪፌ ደሴት ላይ ወደ ሚገኝ ሆስፒታል ተወስደዋል
በስፔን ካናሪ ደሴት ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረች ጀልባ ተገልብጣ የ17 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታወቁ።
ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ጀልባ አርክፔሎኮ የተባለ ስፍራ መዳረሻ ላይ መግለበጧንም ነው ባለስልጣናቱ ያስተወቁት።
ከአደጋው የተረፉ ሶስት ሰዎች በስፔን ጦር ሄሊኮፕተር ቴንሪፌ ደሴት ላይ ወደ ሚገኝ ሆስፒታል ለህክምና መወሰደቸውም የአካባቢው የአደጋ ጊዜ ቢሮ በትዊተር ገጹ አስታውቋል።
ከተረፉ ሶስት ሰዎች መካከል አንደኛው በመጠጥ ውሃ እጦት ክፉኛ መጎዳቱንም ገልጸዋል።
የስፔን የባህር የነብስ አድን አገልግሎት ቢሮ ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት፤ ስደተኞችን ጭና የተገለበጠችውን ጀልባ የስፔን አየር ኃይል ነው በትናትናው እለት በደቡብ ምስራቅ ኤል ሄይሮ
ቀድሞ የተመለከተው።
ይህንን ተከትሎም የነብስ አድን ሰራተኞች እና ጀልባዎች ወደ ስፍራው መላካቸውንም ተናግረዋል።
በጀልባዋ ላይ ተሳፍረው የነበሩ ሁሉም ስደተኞች ከሰሃራ በታች ከሚገኙ የአፍሪካ ሀገራጥ የተነሱ መሆናቸውን በመግለጽ፤ ጀልበዋ ከየት እንደተነሳች ግን እስካሁን አልታወቀም ብለዋል።
በያዝነው ወር መጀመሪያ አካባቢም በደቡብ ኤል ሄይሮ 23 ስደተኞችን ያሳፈረች ጀልባ ላይ የ4 ስደተኞች ህይወት ማለፉንም አስታውሰዋል።