አሜሪካ በአንድ ቀን ብቻ 1,783 ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሞቱባት
አሜሪካ በአንድ ቀን ብቻ 1,783 ዜጎቿ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሞቱባት
በአሜሪካ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ 1,783 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህይወታቸውን አጥተዋል፡፡
በአሜሪካ እስካሁን 16,478 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት የሞቱ ሲሆን 456,828 የሚሆኑት ደግሞ በቫይረሱ መጠቃታቸውን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ያወጣው መረጃ ያመለክታል፡፡
በአሜሪካ በየቀኑ 100,000 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እየተደረገላቸው መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
በአሜሪካ እስካሁን ሁለት ሚሊዮን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ መደረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
ኮሮና ቫይረስ ከአውሮፓዎቹ ጣሊያንና ስፔን ቀጥሎ በትሩን ያሳረፈባት አሜሪካ የማቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገምቷል፡፡
ፕሬዘዳንት ትራምፕ ለኮሮና ቫይረስ መስፋፋት የአለም ጤና ድርጅት አመራር ላይ ያነጣጠረ ትችት እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡
ትራምፕ ድርጅቱ ለቻይና ያዳላ ነው፤ ስለሆነም አሜሪካ ለድርጅቱ የምታደርገውን በጀት ታቋርጣለች ብለው አስፈራርተዋል፡፡ የአለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም በበኩላቸው ትችቱ ተገቢ አለመሆኑንና ድርጅት ፍትሀዊ የሆነ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ባለፈው ታህሳስ ወር ከቻይናዋ ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰው ቫይረሱ እስካሁን ከ95ሺ በለይ ለሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን የወርልዶ ሜትር መረጃ ያሳያል፡፡