የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴድሮስ በ21ኛው ክፍለዘመን ዘረኛ አስተያየቶችን ከሳይንቲስቶች መስማት ነውር ነው ብለዋል
የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄነራል ዶ/ር ቴድሮስ በ21ኛው ክፍለዘመን ዘረኛ አስተያየቶችን ከሳይንቲስቶች መስማት ነውር ነው ብለዋል
የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክትር ጄነራል ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የኮሮና ቫይረስ ክትባት በአፈሪካ ይሞከር ያሉትን የፈረንሳይ ሳይንቲስቶች በጽኑ አወገዙ፡፡
ዶ/ር ቴድሮስ በኮረና ቫይረስ ጉዳይ መግለጫ በሰጡበት ወቅት “ሳይንቲስቶቹ የአዲሱ ክትባት መሞከሪየ ቦታ አፍሪካ ይሆናል ብለው አስተያየት ስጥተዋል፡፡ እውነት ለመናገር በጣም ተከፍቻለሁ” ብለዋል፡፡
“መተባበር ያስፈልጋል እያልኩ በነበረበት ሰአት እንደዚህ አይነት ዘረኛ አስተያየቶች በርግጥ አይጠቅሙም፡፡ይህ የመተባበር ተቃራኒ ነው፤ አፍሪካ ለማንኛውም አይነት ክትባት መሞከሪያ መሆን አትችልም፤ ወደፊትም አይሆንም” በማለት ዶ/ር ቴድሮስ ሳይንቲስቶቹን አውግዘዋል፡፡
አውሮፓ ይሁንአፍሪካ ወይም ሌላ ቦታ መድሀኒት ስንሞክር ተመሳሳይ ህጎችን ነው የምንጠቀመው፡፡ መሞከር ካስፈለገም በተመሳሳይ መንገድ ሁሉም ሰዎች እኩል በማየት ይከናወናል፡፡
በ21ኛው ክፍለዘመን ዘረኛ አስተያተያቶች ከሳይንቲስቶች መስማት ነውር ነው ያሉት ዶ/ር ቴድሮስ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ ስካር መቆም አለበት ብለዋል፡፡
“ይህን በጽኑ እናወግዛለን፡፡ ማረጋገጥ የምንፈልገው ነገር ይህ በአፍሪካ እንደማይደረግ እናረጋግጥላችኋለን፡፡ ሌላ ቦታም በየትኛው ሀገር አይደረግም፤ ትክክለኛ አካሄዶች መተግበር አለባቸው፤ ሰዎች እንደ ሰዎች መታየት አለብን ምክንያቱም ሁላችንም ሰዎች ነን፡፡”