ኬንያ ከናይሮቢ ወደ ውስጥና ወደ ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ማገዷን ፕሬዘዳንት ኡሁሩ አስታወቁ
ኬንያ ከናይሮቢ ወደ ውስጥና ወደ ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ማገዷን ፕሬዘዳንት ኡሁሩ አስታወቁ
የኬንያው ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከኬንያ ዋና ከተማ ናይሮቢ ወደ ውጭና ከውጭ ወደ ውስጥ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ለ21 ቀናት ማገዳቸውን የሀገሪቱ ጋዜጣ ዴይሊ ኔሽን ዘግቧል፡፡
በኬንያ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ስድስት ሰዎች የሞቱ ሲሆን ሌሎች 158 የሚሆኑ ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡
ፕሬዘዳንት ኬንያታ 16 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸውንና ይህም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 158 ከፍ አድርጎታል ብለዋል፡፡
በኬንያ እስካሁን 4277 ሰዎች ምርመራ ተደርጎላቸዋል፡፡ባለፈው ታህሳስ ወር በቻይና ሁቤ ግዛት የተቀሰቀሰው የኮሮና ቫይረስ ወረርስኝ ሀሉንም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አዳርሷል፡፡
ኮሮና ቫይረስ እስካሁን 70,626 ለሆኑ ሰዎች ሞት ምክንያት መሆኑን የወርልዶሜትር መረጃ ያሳያል፡፡ እንደወርልዶሜትር መረጃ ከሆነ እስካሁን 1,289,820 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 272,118 ሰዎች አገግመው ከቫይረሱ ነፃ ሆነዋል፡፡