በአሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት በሚገኝ የእንሰሳት ማቆያ ውስጥ የምትገኝ ነብር በኮሮና ቫይረስ ተያዘች
በአሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት በሚገኝ የእንሰሳት ማቆያ ውስጥ የምትገኝ ነብር በኮሮና ቫይረስ ተያዘች
በአሜሪካ ኒው ዮርክ ግዛት ውስጥ በሚገኝ ብሮንክስ በተባለ የእንሰሳት ማቆያ ማእከል ውስጥ የምትገኝ አንዲት ነብር በተደረገላት ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዟ ተረጋግጧል፡፡
የአራት አመት እድሜ ያላት ነብር ደረቅ ሳል መሳል ከጀመረች በኋላ በተደረገላት ምርመራ መሆኑን የብሮንክስ እንሰሳት ማቆያ ባወጣው መግላጫ ማስታወቁን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡
ከነብሯ ናሙና የተወሰደው ሌሎች አምስት ነብሮችና አንበሶች የመተንፈሻ አካላት በሽታ ምልክት ማሳየት መጀመራቸውን ተከትሎ መሆኑን የአሜሪካ የግብርና ዲፓርትመት ገልጿል፡፡
በእንሰሳት ማቆያው የሚገኙት ሌሎች እንሰሳት ምልክት አላሳዩም ተብሏል፡
በእንሰሳት ማቆያ ውስጥ የሚገኙት ሌሎች እንሰሳት ምንም እንኳን የምግብ ፋላጎት መቀነስ ቢያሳዩም ጤነኛ ናቸው፤ እንክብካቤም እየተደረገላቸው መሆኑን ማቆያ ማእከሉ አስታውቋል፡፡
ቫይረሱ እንዴት በእንሰሳው ላይ እንደተከሰተ የቅርብ ክትትል እየተደረገ መሆኑን ማእከሉ አስታውቋል፡፡