በደቡብ ኮሪያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከስክሶ የ179 ሰዎች ህይወት አለፈ
ከታይላንድ ወደ ደቡብ ኮሪያ ይበር የነበረ የመንገደኞች አውሮፕላን ሙዓን ተብሎ በሚጠራ ቦታ ተከስክሷል
ከ181 መንገደኞች ውስጥ ሁለት ተሳፋሪዎች ብቻ በህይወት ተርፈዋል
በደቡብ ኮሪያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከስክሶ የ179 ሰዎች ህይወት አለፈ።
ቦይንግ ሰራሽ እና የጀጁ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የበረራ መስመሩ 7ሲ2216 የተሰኘ አውሮፕላን በደቡብ ኮሪያ ተከስክሷል።
ቦይንግ 737-800 ስያሜ ያለው አውሮፕላኑ የበረራ አስተናጋጆችን ጨምሮ 181 መንገደኞችን ከታይላንድ ባንኮጭ ጭኖ እየበረረ እያለ በደቡብ ኮሪያዋ ሙዓን ኤርፖርት ለማረፍ ሲሞክር ተከስክሷል ተብሏል።
እስካሁን በወጡ ቅድመ ሪፖርቶች መሰረት 179 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ሁለት ሰዎች ደግሞ በህይወት ተርፈዋል ተብሏል።
የደቡብ ኮሪያ የአደጋ ጊዜ ተቋማት በአውሮፕላኑ ውስጥ ተጨማሪ መንገደኞችን ህይወት ለመታደግ እየጣሩ እንደሆነ የደቡብ ኮሪያ ዜና ወኪል የሆነው ዮናፕ ዘግቧል።
ጀጁ አየር መንገድ እስካሁን ስለ አደጋው መግለጫ ያላወጣ ሲሆን በአደጋው ህይወታቸውን ያጡ መንገደኞች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ተገልጿል።
ቦይንግ እና የአሜሪካ አቪዬሽን በደቡብ ኮሪያ ስለተከሰከሰው የአውሮፕላን አደጋ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
ከአንድ ሳምንት በፊት የአዛርባጂያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን ከባኩ ወደ ሞስኮ በመብረር ላይ እያለ መከስከሱ ይታወሳል።
በአደጋው 38 ሰዎች ሞተዋል የተባለ ሲሆን አውሮፕላኑ በሩሲያ ሚሳኤል ተመቶ እንደወደቀ ዘግይተው በወጡ ሪፖርቶች ላይ ተጠቅሷል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን የአዛርባጂያ ህዝብ እና መንግስትን ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን በወቅቱ ጦራቸው ከዩክሬን የተተኮሱ ድሮኖችን በማምከን ላይ ነበሩም ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራዎች በመደረግ ላይ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንት ፑቲን ተጠያቂነት እንደሚኖርም ተናግረዋል።ቦይንግ ሰራሽ እና የጀጁ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የበረራ መስመሩ 7ሲ2216 የተሰኘ አውሮፕላን በደቡብ ኮሪያ ተከስክሷል።
ቦይንግ 737-800 ስያሜ ያለው አውሮፕላኑ የበረራ አስተናጋጆችን ጨምሮ 181 መንገደኞችን ከታይላንድ ባንኮጭ ጭኖ እየበረረ እያለ በደቡብ ኮሪያዋ ሙዓን ኤርፖርት ለማረፍ ሲሞክር ተከስክሷል ተብሏል።
እስካሁን በወጡ ቅድመ ሪፖርቶች መሰረት 179 ሰዎች መሞታቸው ሲረጋገጥ ሁለት ሰዎች ደግሞ በህይወት ተርፈዋል ተብሏል።
የደቡብ ኮሪያ የአደጋ ጊዜ ተቋማት የአውሮፕላኑን አደጋ ምክንያት እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ ምርመራ እያደረጉ እንደሆነ የደቡብ ኮሪያ ዜና ወኪል የሆነው ዮናፕ ዘግቧል።
ጀጁ አየር መንገድ እስካሁን ስለ አደጋው መግለጫ ያላወጣ ሲሆን የአደጋውን ትክክለኛ ምክንያት ለማወቅ ሪፖርቶችን እያየ መሆኑን ገልጿል።
ቦይንግ እና የአሜሪካ አቪዬሽን በደቡብ ኮሪያ ስለተከሰከሰው የአውሮፕላን አደጋ እስካሁን ያሉት ነገር የለም።
ከአንድ ሳምንት በፊት የአዛርባጂያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ የመንገደኞች አውሮፕላን ከባኩ ወደ ሞስኮ በመብረር ላይ እያለ መከስከሱ ይታወሳል።
በአደጋው 38 ሰዎች ሞተዋል የተባለ ሲሆን አውሮፕላኑ በሩሲያ ሚሳኤል ተመቶ እንደወደቀ ዘግይተው በወጡ ሪፖርቶች ላይ ተጠቅሷል።
ፕሬዝዳንት ፑቲን የአዛርባጂያ ህዝብ እና መንግስትን ይቅርታ የጠየቁ ሲሆን በወቅቱ ጦራቸው ከዩክሬን የተተኮሱ ድሮኖችን በማምከን ላይ ነበሩም ብለዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ ተጨማሪ ምርመራዎች በመደረግ ላይ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንት ፑቲን ተጠያቂነት እንደሚኖርም ተናግረዋል።