የተባበሩት አረብ ኢምሬት ለጡረተኞች የመኖሪያ ፈቃድ እንደምትሰጥ ገለጸች
ዩኤኢ ከ192 ሀገራት በላይ የተሳፉበት ኤክስፖ አዘጋጀች
ሀገሪቱ ሰው አልባ ተሸከርካሪዎች በጎዳናዎቿ እንዲጓዙም ፈቅዳለች
የተባበሩት አረብ ኢምሬት ለውጭ ሀገር ጡረተኛ ዜጎች የመኖሪያ ፈቃድ እንደምትሰጥ ገለጸች፡፡
የዱባዩ ገዢ ሼክ ሞሀመድ ቢን ራሺድ እንደተናገሩት ሀገራቸው የጡረታ ጊዜያቸውን በተባበሩት አረብ ኢምሬት ማሳለፍ ለሚፈልጉ ጡረተኞች የመኖሪያ ፈቃድ ትሰጣለች ብለዋል፡፡
ገዢው የሄንን የተናገሩት ዛሬ የዱባይ ኤክስፖ 2020 አንድ አካል በሆነው የሰው አልባ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስራ ለማስገባት በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ነው፡፡
ገዢው አክለውም “እድሜ ልካቸውን በስራ ሲደክሙ የቆዩ የዓለማችን አገራት ዜጎች ወደ ተባበሩት አረብ ኢምሬት መጥተው ቀሪ የጡረታ ጊዜያቸውን እንዲያሳልፉ የመኖሪያ ፈቃድ እንሰጣለን ኑ አብራችሁን ኑሩ” ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡
የሀገሪቱ ካቢኔ የማንኛውም አገር ዜጋ ሆነው ጡረታ የወጡ ዜጎች ቀሪ የእረፍት ጊዜያቸውን በተባበሩት አረብ ኢምሬት ማሳለፍ ከፈለጉ የመኖሪያ ፈቃድ መስጠት የሚያስችል ህግ ማጽደቁም ተገልጿል፡፡
ዩኤኢ ዱባይ ኤክስፖ 2020 በማዘጋጅት ከ192 በላይ ሀገራት ለገበያ የሚገናኙበትን እድል ፈጥራለች፤ከ25 ሚሊዮን በላይ ሰዎችም በኤክስፖው ላይ ይገኛል፡፡