ዩኤኢ ዲፕሎማቶቿን ከሊባኖስ ያስወጣችው የሊባኖሱ ሚኒስትር “ተቀባይነት የሌለው ንግግር”ማድረጋውን ተከትሎ ነው
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከሊባኖስ ሪፐብሊክ ዲፕሎማቶቿን ማስወጣቷን አስታውቀለች፡፡
የዩኤኢ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ከሊፋ ሸሂን አል ማራር ዩኤኢ ዲሎማቶቿን ለማስወጣት የሰወነችው ጥቂት የሊባኖስ ባለስለጣናት ሳኡዲ አረቢያን የተመለከተ “ተቀባይነት የሌለው ንግግር” ማድረጋውቸን ተከትሎ ለሳኡዲ አረቢያ አጋርነት ለማሳየት መሆኑን ተናረዋል፡፡
ሚኒስቴር ዲኤታው እንደገለጹት የቪዛ ስራው ቤሩት ውስጥ ባለው ኮንሱላር ሴክሽን ስራው ይቀጥላል ብለዋል፡፡
ዩኤኢ ዜጎቿ ወደ ሊባኖስ እንዳይሄዱ እግድ መጣሏንም ተናግረዋል፡፡ የሊባኖስ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ጆርጅ ኮራዲ ባወጡት መግለጫ ሳኡዲ አረቢያና ዩኤኢ በየመን እያደረጉ ያሉትን ተችተዋል፡፡
ይህን መግለጫ ተከትሎ በሊባኖስ የነበሩት የሳኡዲ አረቢያ፣ዬኤኢ፣የኩየት እና የባህሬን ወደየሀገራቸው ተጠርተዋል፤ የሊባኖስ ሚኒስትሩን ጥሩ ያልሆነ መግጫም ተቃውመዋል፡፡