የአከባቢው ጎሳዎች መሳርያ የታጠቁ መሆናቸው ግጭቶቹ እንዲባባስ ምክንያት መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ
በሱዳን ምዕራብ ኮርዶፋ በተከሰተ የጎሳ ግጨት ምክንያት የ20 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ፤ በርካቶች መቁሰላቸው ተሰማ።
በርካቶችን ለህልፈት የዳረገው ግጭት በዓረቦቹ አል-ሃማር እና ሚሰርያ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረ እንደሆነም ነው የአይን እማኞች ለአል-ዐይን የተናገሩት።
የአይን እማኞቹ አል-ማህፉራ በተባለ ስፍራ የግብርና መሬት ልማትን ምክንያት በማድረግ በሁለት ቤተሰቦች መካካል የተነሳው ግጭት ከመንግስት ኃይሎች ውጭ ሆኖ በፍጥነት በመስፋፋት የጎሳ ግጭት ቅርፅ መያዝ መቻሉን ተናግረዋል።
በአከባቢው በመሬት የተነሳ በዝናባማ ወቅቶች መሰል ግጭቶች ሲያጋጥሙ የመጀመርያ ባይሆንም ይሄኛው የከፋ ከሚባሉትመሆኑም ታውቋል።
በምዕራብ ኮርዶፋ የሚገኙ የተለያዩ ጎሳዎች ከቀላል እስከ ከባድ መሳርያ የታጠቁ በመሆናቸው መሰል ግጭቶች ሲነሱ ነገሮች ወደ ከፋ መንገድ እንዲያመሩ ትልቅና አሉታዊ ሚና መጫወቱንም ነው መረጃዎች የሚያመላክቱት።