በቀጠለው የእስራኤል ጥቃት በራፋ 20 ሰዎች ተገደሉ
በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች ከእስራኤል ጥቃት ለማምለጥ ጋዛን ከግብጽ ጋር በሚያዋስነው ራፋ ተጨናንቀው ይገኛሉ
ተኩስ ይቁም የሚል የውሳኔ ሀሳብ በተመድ የጸጥታው ምክርቤት ቢቀርብም፣ በአሜሪካ ተቃውሞ ሳይጸድቅ መቅረቱ ይታወሳል
በቀጠለው የእስራእፈል ጥቃት በራፋ 20 ሰዎች ተገደሉ።
እስራኤል በደቡባዊ ጋዛ በራፋ አካባቢ የሚገኙ ሶስት ቤቶችን መትታ 20 ሰዎችን መግደሏን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር ባለስልጣናት በዛሬው እለት አስታውቋል።
በ10ሺዎች የሚቆጠሩ የጋዛ ነዋሪዎች ከእስራኤል ጥቃት ለማምለጥ ጋዛን ከግብጽ ጋር በሚያዋስነው ራፋ ተጨናንቀው ይገኛሉ።
ሮይተርስ የካን ዮኒስ ነዋሪዎችን ጠቅሶ እንደዘገው በዛሬው እለት ጠዋት በእስራኤል ጦር እና በሀማስ ታጣቂዎች መካከል ከባድ የተኩስ ልውውጥ ተካሂዷል።
ነዋሪዎቹ እንዳሉት የእስራኤል ታንክ እና የጦር አውሮፕላኖች የከተማዋን መሀል ደብድበዋል።
የአለም ጤና ድርድት ባለስልጣን እንደተናገሩት የእስራኤል ወታደሮች ባለፈው ሳምንት የወረሩት በሰሜን ጋዛ የሚገኘው ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ማቆሙን እና ህጻናትን ጨምሮ ታካሚዎች ለቀው እንዲወጡ ተገደዋል።
"ሆስፒታሎችን ማጣት አይገባንም" ሲሉ በጋዛ የድርጅቱ ተወካይ ሪቻርድ ፒፐርኮርን ተናግረዋል።
እስራል ጥቃት አጠናክራ በቀጠለችበት ካን ዮኒስ በሚገኘው ናሰር ሜዲካል ኮምሌክስ ቤዝመንት ውስጥ ከ4ሺ በላይ ተፈናቃዮች ተጠልለው እንደሚገኙ ተናግረዋል።
የጋዛ ጤና ሚኒስቴር እንደገለጸው ከተጀመረ ሁለት ወራት ባስቆጠረው ጦርነት 19ሺ በላይ ፍልስጤማውያን ተገድለዋል፤ 52ሺ በላይ ደግሞ ቆስለዋል።
ሀማስ ድንበሯን ጥሶ ጥቃት የፈጸመባት እስራኤል ሀማስን ከምድረገጽ አጠፋለሁ ብላ ዝታለች።
በጋዛ በጦርነቱ ምክንያት የሰብአዊ ቀውስ ስለተባባስ ተኩስ ይቁም የሚል የውሳኔ ሀሳብ በተመድ የጸጥታው ምክርቤት ቢቀርብም፣ በአሜሪካ ተቃውሞ ሳይጸድቅ መቅረቱ ይታወሳል።