እስራኤላዊያን ድርጊቱን የተቃወሙ ሲሆን መንግስታቸው የታገቱ ዜጎች በድርድር እንዲያስቅቅ ጠይቀዋል
እስራኤል በስህተት የራሷን ዜጎች መግደሏን ገለጸች፡፡
ለፍልስጤም ነጻነት እንደሚዋጋ የሚገልጸው ሀማስ ከ70 ቀናት በፊት በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት ማድረሱን ተከትሎ በአካባቢው ጦርነት ተቀስቅሷል።
ይህን ተከትሎም እስራኤል የአጸፋ እርምጃ የጀመረችው ዘመቻ አሁንም የቀጠለ ሲሆን እስካሁን 19 ሺህ ፍልስጤማዊያን ተገድለዋል።
በሐማስ የታገቱ እስራኤላዊያንን ለማስለቀቅ በሚል እግረኛ ወታደሮቿን ወደ ጋዛ የላከችው እስራኤል በስህተት ሶስት ዜጎቿን እንደገደለች ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የእስራኤል ጦር ሶስቱን እስራኤላዊንን የገደለው በስህተት ጠላት መስለውት እንደሆነ አስታውቋል፡፡
በስህተት ተገደሉ የተባሉት ሶቱ እስራኤላዊያን የ28፣ የ26 እና የ22 ዓመት ወጣቶች ናቸው የተባለ ሲሆን ከ70 ቀን በፊት በሐማስ ታግተው እንደተወሰዱ ተገልጿል፡፡
ይህን ተከትሎም በርካታ ሀገራት እና እስራኤላዊያን የሀገሪቱን ጦር ድርጊት የተቹ ሲሆን የታገቱ ዜጎች በድርድር እንዲለቀቁ ግፊት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
እስራኤልን ኮንነው አስተያየት በመስጠት ላይ የነበሩ የቱርክ ፓርላማ አባል በልብ ህመም ህይወታቸው አለፈ
የእስራኤል ጦር አስከሬን ሳይሆን ዜጎቻችንን ከነ ህይወታቸው ያምጣልን ሲሉ በርካታ ዜጎች በማህበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት እየጻፉ ናቸው ተብሏል፡፡
ለእስራኤል የቀጥታ የጦር መሳሪያ ድጋፍ በማድረግ ላይ ያለችው አሜሪካ አሁን ላይ እስራኤል በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ጠይቃለች።
ፕሬዝዳንት ባይደን ከሰሞኑ ባደረጉት ንግግር እስራኤል ያላት ዓለም አቀፍ ድጋፍ እየቀነሰ ነው፣ የተኩስ አቁም እንዲደረግ ለጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁም ነግሬዋለሁ ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን ጨምሮ በርካታ የዓለማች ሀገራት እስራኤል የተኩስ አቁም እንዲታወጅ ግፊት በማድረግ ላይ ሲሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በጦር ወንጀል እንዲጠየቁ በመወትወት ላይ ናቸው፡፡
እስራኤል በበኩሏ ከ70 ቀን በፊት በሐማስ ታግተው ከተወሰዱ ዜጎች ውስጥ 70 ዜጎች እስካሁን እንዳልተለቀቁ አስታውቃለች፡፡