ጋዜጠኝነት - በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት
73ኛ ቀኑን በያዘው የእስራኤልና ሃማስ ጦርነት ከ60 በላይ ጋዜጠኞችና የካሜራ ባለሙያዎች ተገድለዋል
እስራኤል በጋዛ በምትፈጽመው ድብደባ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የደህንነት ዋስትና እንደማትሰጥ ገልጻለች
የእስራኤልና ሃማስ ጦርነት ዛሬ 73ኛ ቀኑን ይዟል።
በጦርነቱ ከ19 ሺህ በላይ ፍልስጤማውያን እና ከ1 ሺህ 200 በላይ እስራኤላውያን ህይወት አልፏል።
በጋዛ እና በሊባኖስ ድንበር ያለውን ሁኔታ ለአለም የሚያደርሱ ከ60 በላይ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችም ህይወታቸው መቀጠፉን የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ ባወጣው መግለጫ አመላክቷል።
እስራኤል በጋዛ በምትፈጽመው ድብደባ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የደህንነት ዋስትና ከመከልከሏ ባሻገር ጋዜጠኖችን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶች ትፈጽማለች የሚል ክስ ቀርቦባታል።
ሲፒጄ በስም ዝርዝሮ ያቀረባቸው ህይወታቸው ያለፈ ጋዜጠኞችና የካሜራ ባለሙያዎች ቁጥር 64 ነው ቢባልም የፍልስጤማ ባለስልጣናት ግን በጋዛ ብቻ 92 ጋዜጠኖች መገደላቸውን ተናግረዋል ብሏል አናዶሉ በዘገባው።