በአሜሪካ ባለፉት ስድስት ወራት ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች በትራፊክ እደጋ ህይወታቸው ማለፉ ተገለጸ
የዘንድሮው የሟቾች ቁጥር ባለፉት 16 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው ተብሏል
በርካታ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ቤት መቆየታቸው ለአደጋው መጨመር ምክንያት ሆኗል ተብሏል
በአሜሪካ ባለፉት ስድስት ወራት ከ20 ሺህ በላይ ሰዎች በትራፊክ እደጋ መሞታቸው ተገለጸ፡፡
የአሜሪካ ትራፊክ ቁጥጥር እንዳስታወቀው በተያዘው የ2022 ዓመት ውስጥ ባሉ ስድስት ወራት ውስጥ በትራፊክ አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 20 ሺህ 175 ደርሷል፡፡
የሟቾች ቁጥር ባለፉት 16 ዓመታት ውስጥ ከፍተኛው ነው የተባለ ሲሆን በኮሮና ቫይረስ መስፋፋት ምክንያት ብዙ ሰዎች ከእንቅስቀሴ ውጪ መቆየታቸው ለአደጋው መጨመር አንዱ ምክንያት ሊሆን ይችላል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
አሽከርካሪዎች የደህንነት ቀበቶ ሳያደርጉ መንዳት እና ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ የታዩ ከፍተኛ የትራፊክ ጥሰቶች ናቸው ተብሏል፡፡
በ2021 ዓመት በአሜሪካ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ዜጎች ቁጥር 7 ሺህ 242 ብቻ የነበረ ሲሆን አደጋው በዚህ ዓመት ከፍተኛ የሚባል ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
ከሟቾች ውስጥ 985 ያህሉ ሞተረኞች ሲሆኑ ቀሪዎቹ እግረኞች እና አሽከርካሪዎች ነበሩም ተብሏል፡፡
የአሜሪካ የፈጣን መንገዶች ባለስልጣን የሀላፊነት ቦታ ከቀድሞው የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአስተዳደድር ጊዜ ጀምሮ ክፍት ሲሆን የወቅቱ ፕሬዝዳንት ባይደን ይሄንን ክፍተት እንዲሞሉ ተጠይቀዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳድር የትራፊክ አደጋን እንደ ዋነኛ ሀገሪቱ የደህንነት ችግር አድርገው እንዲመለከቱት የተለያዩ አካላት በመወትወት ላይ እንደሆኑም በዘገባው ላይ ተጠቅሷል፡፡